Egir Awetah

ምነው እግር አወጣህ እንዴት ፈረደብኝ
ያም አንተን ያም አንተን አየሁት በዛብኝ
ወዴት ነው መዋያህ ፈራሁኝ እንጃልኝ
አይን በዝቶብሃል ሽሽግ በልልኝ
አይን በዝቶብሃል ሽሽግ በልልኝ

ፍቅር የብር ጌጥ አሰራህ
ፍቅር ይልሃል መንደሩ
ፍቅር ይልቅ ያንተ ገላ
ፍቅር አይሆንም ወይ ጥሩ
ፍቅር ከረባት አስረሃል
ፍቅር ብለው አወሩልኝ
ፍቅር ካንገቱ አያስንቅም
ፍቅርን አውልቀው በሉልኝ

ከእግር እስከ ራስህ እንዳሳየሀቸው
አይንህን ጥርስህን ግድ የለም በላቸው
ልየው ያሉ እንደሆነ
በለመደ አይናቸው
ልብህን አደራ የሷ ነው በላቸው
ልብህን አደራ የሷ ነው በላቸው

ፍቅር አይን አይከለከል
ፍቅር ያየ ሰው ይመኛል
ፍቅር የኔ መሆንህን
ፍቅር ማን ይረዳልኛል
ፍቅር እዛም እዛም አትበል
ፍቅር ፍርሃት አደረብኝ
ፍቅር ልብህን መርምረው
ፍቅር እንዳያገኙብኝ

ምነው እግር አወጣህ እንዴት ፈረደብኝ
ያም አንተን ያም አንተን አየሁት በዛብኝ
ወዴት ነው መዋያህ ፈራሁኝ እንጃልኝ
አይን በዝቶብሃል ሽሽግ በልልኝ
አይን በዝቶብሃል ሽሽግ በልልኝ

ፍቅር የብርጌጥ አሰራህ
ፍቅር ይሉሃል መንደሩ
ፍቅር ይልቅ ያንተ ገላ
ፍቅር አይሆንም ወይ ጥሩ
ፍቅር አይን አይከለከል
ፍቅር ያየሰው ይመኛል
ፍቅር የኔ መሆንህን
ፍቅር ማን ይረዳልኛል



Credits
Writer(s): Aster Aweke
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link