Kaguwaguwazegne

ካጓጓዘኝ ጎዳናው መንገዱ
ይፍረስ ቤቴ ግራር እና ፅዱ
ምን ጓዝ አለ ሰው ወደው ሲሄዱ
ካጓጓዘኝ ጎዳናው መንገዱ
ይፍረስ ቤቴ ግራር እና ፅዱ
ምን ጓዝ አለ ሰው ወደው ሲሄዱ

የድንገት ትውውቅ የምሽት የማታ አሄ
ሸለመኝ ለፍቅር የአንድ ቀን ሰላምታ አሄ
የልቤ ምግብ ነው ሳቅና ጨዋታሽ
ደስታና ፈገግታሽ
እንደ ጥልፍ አጣፊ እንደ ኩታ ለባሽ አሄ
ጥበቡን ደርቦ ማን ከሆዴ አስገባሽ አሄ
በፍቅር መንገድ ላይ ይከፋል ትዝታ
ነይ ነይ የኔ አውታታ

ካጓጓዘኝ ጎዳናው መንገዱ
ይፍረስ ቤቴ ግራር እና ፅዱ
ምን ጓዝ አለ ሰው ወደው ሲሄዱ
ካጓጓዘኝ ጎዳናው መንገዱ
ይፍረስ ቤቴ ግራር እና ፅዱ
ምን ጓዝ አለ ሰው ወደው ሲሄዱ

ሽመላማው ገላ ፍቅሯን እያደለኝ አሄ
ተሸነፈ ልቤ እያደረ ጣለኝ አሄ
ቢያሸበርቅ ነው ወይ ቢደራ ገላሽ
አንጀቴን በላሽ
ነገር አያቀና እኔማ ብልሃቴ አሄ
ሰው ባፈቅር ከዳኝ ድፍን አካላቴ አሄ
ማተቤን ለፍቅር በጥሼው ካንገቴ
ናፍቆት ሆነ ዕርስቴ

ካጓጓዘኝ ጎዳናው መንገዱ
ይፍረስ ቤቴ ግራር እና ፅዱ
ምን ጓዝ አለ ሰው ወደው ሲሄዱ
ካጓጓዘኝ ጎዳናው መንገዱ
ይፍረስ ቤቴ ግራር እና ፅዱ
ምን ጓዝ አለ ሰው ወደው ሲሄዱ

በታጎለ ጉዞሽ የመለያየቱ ኡሁ
ልቤ ሰው አይሸኝም አይችልም አንጀቱ አሄ
ምነው ብቸኝነት ግዞት ያለ ዳኛ
ነይልኝ እይኛ
ልቤም ልቡን ካጣ ሆዴም ሆድ ከባሰው አሄ
ናፍቆት ቀንበር ጠምዶ አንጀቴን ካረሰው አሄ
እርሜን ላውጣ እንግዲ ወዳጅ ከተለየው
ማጣት የታደለኝ
እርሜን ላውጣ እንግዲ ወዳጅ ከተለየው
ማጣት የታደለኝ



Credits
Writer(s): Elias Woldemariam, Yilma G/ab
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link