Geday Neh

ገዳይ ነህ ገዳይ ነህ
በፍቅር ገዳይ ነህ
ገዳይ ነህ ገዳይ ነህ
በመውደድ ገዳይ ነህ
ሳትተኩስ የምትገድል
የልጅ አርበኛ ነህ
ሳትተኩስ የምትገድል
የልጅ አርበኛ ነህ
ሞቻለሁ ሞቻለሁ
በፍቅርህ ሞቻለሁ
ሞቻለሁ ሞቻለሁ
በመውደድ ሞቻለሁ
ነፍስ እንድትዘራብኝ
እማፀንሃለው
ነፍስ እንድትዘራብኝ
እማፀንሃለው
እንደ አሻንጉሊቱ እንደ ሰው ሰራሹ
አፍርሰህ ምትሰራኝ የአምላክ ታናሹ
ወንዳወንድ አልኩና ሰጠሁህ ስያሜ
ማስረዘም ማሳጠር ችለሃል የኔን እድሜ
ማስረዘም ማሳጠር ችለሃል የኔን እድሜ
ገሎ ማዳኑንም ትችላለህ አሉ
የሞተን ማስነሳት ትችላለህ አሉ
ገሎ ማዳኑንም ትችላለህ አሉ
የሞተን ማስነሳት ትችላለህ አሉ
ምናለ ብትመልሰኝ ብትሰራኝ በውሉ
ምናለ ብትመልሰኝ ብትሰራኝ በውሉ
እንደ አሻንጉሊቱ እንደ ሰው ሰራሹ
አፍርሰህ ምትሰራኝ የአምላክ ታናሹ
ወንዳወንድ አልኩና ሰጠሁህ ስያሜ
ማስረዘም ማሳጠር ችለሃል የኔን እድሜ
ማስረዘም ማሳጠር ችለሃል የኔን እድሜ
ወንዳወንድ አልኩና ሰጠሁህ ስያሜ
ማስረዘም ማሳጠር ችለሃል የኔን እድሜ
ማስረዘም ማሳጠር ችለሃል የኔን እድሜ



Credits
Writer(s): Samuel Alemu, Yeshi Demelash Unknown
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link