Eyesus

ትዝ እያለኝ ትውስ እያለኝ
በጻድቃን ጉባዔ ላመልክህ ቆምኩኝ
ትዝ እያለኝ ትውስ እያለኝ
ከሚወዱህ ጋራ ላመልክህ ቆምኩኝ

ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ
ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ

ቸርነትህ የገባው ባንተ የተጎበኘ
ሊወድስህ ሊያከብርህ ባደባባይ ተገኘ
አልቀረም ቁጭ እንዳለ ከችግሩ ተጣብቆ
ያከብርሃል በሰው ፊት ማቁን ከላዩ አውልቆ

ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ
ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ

ወደ አንተ የመጣውን ሁሉን ደህና አድርገህ
አቀርቅሮ እንዳይመለስ ቀንበሩን ትሰብራለህ
መፍትሄ ከታጣለት ተስፋ ከሌለው ጉዳይ
እፎይ አለ ስንቱ ሰው ሆነህለት ገላጋይ

እውራን አይተዋል (ኢየሱስ) ለምጻሞችም ነጹ (ኢየሱስ)
አንካሶች ዘለዋል (ኢየሱስ) ሙታንም ተነሱ (ኢየሱስ)
ክንድህ አልደከመ (ኢየሱስ) ሁሌም ትሰራለህ (ኢየሱስ)
ትናንትናም ዛሬም (ኢየሱስ) ዘላለም ህያው ነህ (ኢየሱስ)

ስላንተማ ይወራ ስላንተማ ይነገር
ለጭቁኑ ባትደርስ እንዴትስ ይሆን ነበር
ውሎ አደረ በሰላም ምህረትህን ተማምኖ
ክብር ያየ በቤትህ አይጠግብም አመስግኖ

ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ
ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ

ትዝ እያለኝ ትውስ እያለኝ
በጻድቃን ጉባዔ ላመልክህ ቆምኩኝ
ትዝ እያለኝ ትውስ እያለኝ
ከሚወዱህ ጋራ ላመልክህ ቆምኩኝ



Credits
Writer(s): Tekeste Getnet
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link