Misiganaye Neh

ተራራው ፡ ከፊቴ ፡ እንደሰም ፡ ቀለጠ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ነህ
ቃልህም ፡ ሲወጣ ፡ ጫካው ፡ ተገለጠ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ነህ
እግሮቼም ፡ ፀኑልኝ ፡ እንደዋላ ፡ እግር ፡ ምሥጋናዬ ፡ ነህ
ረዳት ፡ ሆነኸኛል ፡ አምላኬ ፡ ክበር ፡ ምሥጋናዬ ፡ ነህ

አዝ፦ ልሰዋ ፡ የምሥጋናን ፡ መስዕዋት (፪x)
ሆነኸኝ ፡ አይቻለሁ ፡ አባት (፪x)
ላክብርህ ፡ እኔ ፡ ደጋግሜ (፪x)
ከፍ ፡ በል ፡ ላዚም ፡ ፊትህ ፡ ቆሜ (፪x)
አቤቱ ፡ ተደንቄያለሁኝ ፡ እና (፪x)
ልሰዋ ፡ ምሥጋና (፬x)

ምህረትህ ፡ ከሕይወት ፡ በርግጥም ፡ ይበልጣል ፡ ምሥጋናዬ ፡ ነህ
ደጅ ፡ ጥናት ፡ የለም ፡ በፍጥነት ፡ ያነሳል ፡ ምሥጋናዬ ፡ ነህ
ድንጋይ ፡ ተደርድሮ ፡ ሞት ፡ ሲጠብቃት ፡ ምሥጋናዬ ፡ ነህ
ሀፍረቷን ፡ ሸፍነህ ፡ ሰላም ፡ ሂጂ ፡ አልካት ፡ ምሥጋናዬ ፡ ነህ

አዝ፦ ልሰዋ ፡ የምሥጋናን ፡ መስዕዋት (፪x)
ሆነኸኝ ፡ አይቻለሁ ፡ አባት (፪x)
ላክብርህ ፡ እኔ ፡ ደጋግሜ (፪x)
ከፍ ፡ በል ፡ ላዚም ፡ ፊትህ ፡ ቆሜ (፪x)
አቤቱ ፡ ተደንቄያለሁኝ ፡ እና (፪x)
ልሰዋ ፡ ምሥጋና (፬x)



Credits
Writer(s): Samuel Alemu, Tekeste Getnet
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link