Be Maderiaw Laye

አይጓደልም ፡ ልማዴ
እሰዋለሁኝ፡ ለውዴ
ሆነ ፡ አልሆነ ፡ ነገሩ
አባቴ ፡ አለ ፡ በመንበሩ
አይቋረጥም ፡ ልማዴ
እሰግዳለሁኝ ፡ ለውዴ
ሞላ ፡ አልሞላ ፡ ነገሩ
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በመንበሩ

አዝ፦ በማደሪያው ፡ ላይ
በዙፋኑ ፡ ላይ
በመንበሩ ፡ ላይ
በከፍታው ፡ ላይ
አለ ፡ የሚሰማ ፡ የሚያይ
አለ ፡ የሚረዳ ፡ የሚያይ
አለ ፡ የሚፈውስ ፡ የሚያይ
አለ ፡ የሚረዳ ፡ የሚያይ

መጣሁ ፡ ላመልከው
መጣሁ ፡ ላደናንቀው
መጣሁ ፡ ተመስገን ፡ ልለው
መጣሁ ፡ ፍቅሬን ፡ ልነግረው
ሌላማ ፡ መሻት ፡ የለኝም
ኢየሱስ ፡ ይክበርልኝ
ሌላማ ፡ አምሮት ፡ የለኝም
ኢየሱስ ፡ ይክበርልኝ

አይጓደልም ፡ ልማዴ
እሰግዳለሁኝ ፡ ለውዴ
ሆነ ፡ አልሆነ ፡ ነገሩ
አባቴ ፡ አለ ፡ በመንበሩ
አይቋረጥም ፡ ልማዴ
እሰግዳለሁኝ ፡ ለውዴ
ሞላ ፡ አልሞላ ፡ ነገሩ
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በመንበሩ

አዝ፦ በማደሪያው ፡ ላይ
በዙፋኑ ፡ ላይ
በመንበሩ ፡ ላይ
በከፍታው ፡ ላይ
አለ ፡ የሚሰማ ፡ የሚያይ
አለ ፡ የሚረዳ ፡ የሚያይ
አለ ፡ የሚፈውስ ፡ የሚያይ
አለ ፡ የሚረዳ ፡ የሚያይ

ክበር ፡ ልበልህ ፡ ንገስ ፡ ልበልህ
ያለኝ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ይሄ ፡ ነው
አምልኮን ፡ ላንተ ፡ አበዛለሁ
ያለኝ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ይሄ ፡ ነው
ውዳሴን ፡ ላንተ ፡ አበዛለሁ

ለአስራ ፡ ስምንት ፡ አመታት ፡ መሬት ፡ መሬቱን ፡ እያየች
አቀርቅራ ፡ ምትራመድ ፡ ጎባጣ ፡ ሴት ፡ የነበረች
በቤተመቅደስ ፡ ተገኝታ ፡ ልዑልን ፡ ስታወድሰው
የብዙ ፡ ዓመት ፡ መከራዋን ፡ ከላይዋ ፡ አንከባለለው

አዝ፦ በማደሪያው ፡ ላይ
በዙፋኑ ፡ ላይ
በመንበሩ ፡ ላይ
በከፍታው ፡ ላይ
አለ ፡ የሚሰማ ፡ የሚያይ
አለ ፡ የሚረዳ ፡ የሚያይ
አለ ፡ የሚፈውስ ፡ የሚያይ
አለ ፡ የሚረዳ ፡ የሚያይ



Credits
Writer(s): Samuel Alemu, Tekeste Getnet
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link