Ethiopiaye

አቤቱ በቅን ልጆቿ
ተዘርግተዋል እጆቿ
ከበረከትህ አትለያት
አባት ሆይ በቸር አይንህ እያት
እያት እያት በል እያት
እያት እያት በል እያት
እያት እያት ኢትዮጲያን
እያት እያት በል እያት
እያት እያት አክባሪህን
እያት እያት አትለያት
እያት እያት ባንድነቷ
እያት እያት አቆያት
እያት እያት
የጉያሽ ቁስል ለዘመን ኢትዮጲያ
ሲድን ሲያገረሽ ያመመን ኢትዮጲያ
አይቀርም አልሺን እንዳለ ኢትዮጲያ
አይዞሽ እማማ ቀና በይ ቀን አለ
ኢትዮጲያዬ ኢትዮጲያ
ሰላም ሁኚልኝ እማማ
ኢትዮጲያዬ ኢትዮጲያ
ሰላም ሁኚልኝ እማማ
ፀንቶ በቃል ሳይለያይ
የታሰረው ወገቧ ላይ
ህብረ ቀለሙ ለብርታቷ
የማሪያም ነው መቀነቷ
አምሮ ዙሪያ ገባው
ተከብራ በካባው
አዝመራዋ ሞልቶ በፍሬ
ልጅ አዋቂው ስቆ
እንቦሳው ቦርቆ
ውላ ትደር ሰላም አገሬ
በዝናው
አለም እንዳቀና
ጥበብ የተሞላች አይናማ
የማንነቴ ራስ
ስጋ ደሜ እስትንፋስ
ክብሬ ናት ኢትዮጲያ ሀገሬ እማማ
እማማ እማ
ኢትዮጲያዬ ኢትዮጲያ
ሰላም ሁኚልኝ እማማ
ኢትዮጲያዬ ኢትዮጲያ
ሰላም ሁኚልኝ እማማ
እማማ እማ
አቤቱ በቅን ልጆቿ
ተዘርግተዋል እጆቿ
ከበረከትህ አትለያት
አባት ሆይ በቸር አይንህ እያት
እያት እያት በል እያት
እያት እያት በል እያት
እያት እያት ኢትዮጲያን
እያት እያት በል እያት
እያት እያት አክባሪህን
እያት እያት አትለያት
እያት እያት ባንድነቷ
እያት እያት አቆያት
የጥቁር ህዝቦች ነፃነት ኢትዮጲያ
አምሳለ ፍቅር የአንድነት ኢትዮጲያ
ለተሳለ የሺህ ዝማሬ ኢትዮጲያ
አንቺም እልል በይ ሀገሬ ሀገሬ
ኢትዮጲያዬ ኢትዮጲያ
ሰላም ሁኚልኝ እማማ
ኢትዮጲያዬ ኢትዮጲያ
ሰላም ሁኚልኝ እማማ
በካህናት ቅዱስ ልሳን
በመስጊዱ ፀሎት አዛን
ተደጋግፎ የበረታ
ሚስጥር አላት ያልተፈታ
አምሮ ዙሪያ ገባው
ተከብራ በካባው
አዝመራዋ ሞልቶ በፍሬ
ልጅ አዋቂው ስቆ
እንቦሳው ቦርቆ
ውላ ትደር ሰላም አገሬ
በዝናው
አለም እንዳቀና
ጥበብ የተሞላች አይናማ
የማንነቴ ራስ
ስጋ ደሜ እስትንፋስ
ክብሬ ናት ኢትዮጲያ ሀገሬ እማማ
ኢትዮጲያዬ ኢትዮጲያ
ሰላም ሁኚልኝ እማማ
ኢትዮጲያዬ ኢትዮጲያ
ሰላም ሁኚልኝ እማማ
እማማ እማ
አይያ ኢያ እማማ



Credits
Writer(s): Solomon Ambaw
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link