Minjar (Hageru Sileka)

ሀገር ሲበረበር
ስፍራ ሲበረበር የት ሄደህ ነበር
ሀገር ሲበረበር ሁሉም ሲበረበር
የት ሄደህ ነበር
አገሩ ሲለካ
መንገዱ ሲለካ እሩቅ ነዉ ለካ
ዉበቱ ሲለካ ዉሎዉ ሲለካ
የለዉም ሚሳካ

የንጉስ ወዳጅ ነኝ የጀግና ፍቅረኛ (አሀይ ንቦ)
የጀግና ፍቅረኛ (አሀይ ንቦ)
ቃል ለምድር ለሰማይ ሌላም አያምረኛ (አሀይ ንቦ)
ሌላም አያምረኛ (አሀይ ንቦ)
እንኳን ሰዉነቴ ስለብስ የሚያምርበት (አሀይ ንቦ)
ስለብስ የሚያምርበት (አሀይ ንቦ)
የቀሚሴ ጥለት የሱ ስም አለበት (አሀይ ንቦ)
የሱ ስም አለበት (አሀይ ንቦ)

ፍቅር ጠፋ አትበሉ ፍቅር እንዴት ይጠፋል
ይታዘባል እንጂ እየሳቀ ያልፋል
ንፋስ በነፈሰ ፀሀይ በወጣበት
እንዴታ ይገና ፍቅር የሌለበት

ንቦ ንቦ ንቦ አንተ የማር ገንቦ
ንቦ ንቦ ንቦ አንተ ወርቀ ዘቦ
ንቦ ንቦ ንቦ ዴጓ ላይ ዘንቦ
ዘንቦ ዘንቦ ዘንቦ ባመጣህ ስቦ

ሀገር ሲበረበር
ስፍራ ሲበረበር የት ሄደህ ነበር
ሀገር ሲበረበር ሁሉም ሲበረበር
የት ሄደህ ነበር
አገሩ ሲለካ
መንገዱ ሲለካ እሩቅ ነዉ ለካ
ዉበቱ ሲለካ ዉሎዉ ሲለካ
የለዉም ሚሳካ

የደጋ ሰዉ ፍቅር ሲለዩት ትዝታ (አሀይ ንቦ)
ሲለዩት ትዝታ (አሀይ ንቦ)
ሲተኙ ህልም ነዉ ሲበሉ ስቅታ (አሀይ ንቦ)
ሲበሉ ስቅታ (አሀይ ንቦ)
አይንስ ምን አገባዉ ጥርስስ ምን አገባዉ (አሀይ ንቦ)
ጥርስስ ምን አገባዉ (አሀይ ንቦ)
ልብና ልብ ነዉ ቀድሞ የሚግባባዉ (አሀይ ንቦ)
ቀድሞ የሚግባባዉ (አሀይ ንቦ)

ይምጣ የተማረዉ ፍቅር የተካነዉ
ባወቅንበትን እኛም ባስነካነዉ
በአባቱ ሀይላቸዉ በእናቱ ፈሰሱ
አሳስቆ ገዳይ እንዳንድን በጥርሱ

ንቦ ንቦ ንቦ አንተ የማር ገንቦ
ንቦ ንቦ ንቦ አንተ ወርቀ ዘቦ
ንቦ ንቦ ንቦ ዴጓ ላይ ዘንቦ
ዘንቦ ዘንቦ ዘንቦ ባመጣህ ስቦ

የሀገሬ ጎበዝ የፍቅር ጀግና
ሸብ አርጎኝ ይሂድ እንደ ጀበርና
በአምባ ላይ ፈረስ እየጋለበ
ከተፍ የሚል ነዉ ልቡ እንዳሰበ
የሚያሚናሙን እንደ ባዘቶ
አይገደፍም አንድ ቀን ቀርቶ
ንቦ እንደገና ንቦ አንድ አለብህ
መለስ ቀለስ በል እንዳማረብህ

ንቦ ንቦ ንቦ አንተ የማር ገንቦ
ንቦ ንቦ ንቦ አንተ ወርቀ ዘቦ
ንቦ ንቦ ንቦ ዴጓ ላይ ዘንቦ
ዘንቦ ዘንቦ ዘንቦ ባመጣህ ስቦ

አይብላሃ አይብላህ ወመኔ (አይብላሃ አይብላህ ወመኔ)
አይብላሃ አይብላህ ወመኔ (አይብላሃ አይብላህ ወመኔ)
አይብላሃ አይብላህ ቀማኛ (አይብላሃ አይብላህ ቀማኛ)
አይብላሃ አይንከስህ ጥርሱ (አይብላሃ አይንከስህ ጥርሱ)
አይብላሃ መቼም ከጉልበቱ (አይብላሃ አይብላህ ጉልበቱ)
አይብላሃ ይቀድማል ምላሱ (አይብላሃ ይቀድማል ምላሱ)
አይብላሃ አይብላህ አሞራ (አይብላሃ አይብላህ አሞራ)
አይብላሃ አይብላህ ወመኔ (አይብላሃ አይብላህ ወመኔ)
አይብላሃ ዛሬ ሆዱን እንጂ (አይብላሃ ዛሬ ሆዱን እንጂ)
አይብላሃ መች ያዉቃል ነግ በኔ (አይብላሃ መች ያዉቃል ነግ በኔ)

እንግዲህ እንግዲህ እንግዲህ እንግዲህ
እንግዲህ በል እንግዲህ ያዝ እንግዲህ
እንግዲህ እንግዲህ ሳብ እንግዲህ
እንግዲህ አምጣዉ ወዲህ
አርገዉ ጠበቅ አርገዉ ነጠቅ
አርገዉ ነጠቅ አርገዉ ጨመቅ
አርገዉ መታ አይዞህ በርታ
አርገዉ መታ አታመንታ
አርገዉ ነካ አርገዉ ተካ
ገና ገና መች ተነካ

አርገዉ ወጠር አርገዉ ወጠር
አርገዉ ለኮስ አርገዉ ቆስቆስ
በል እንግዲህ ሳብ እንግዲህ
የለም በቃ ወዲያ ወዲህ
ቁመቱ ዝግባ መል ሶረኔ
መዉደድ ዳኛ ፍቅሩንሰ ለኔ
እያካካሱ የሚያስታርቀዉ
ይዞ የሚያጠብቀዉ
አቅፎ ሚያሞቀዉ
የጦስኝ ቅጠል የደጋግ ቅመም
ከሱ መለየት የአይን ነዉ ህመም



Credits
Writer(s): Hamelmal Abate
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link