Tew Debabsew

በዚች አለም አንተን አፍቅሬያለዉ
እስከዛሬም አብሬህ ኖሬያለዉ
ደስ እንዲልህ ለአንተ ምን ያልሆንኩት አለኝ
እስቲ ይሄ ቀረሽ በለኝ
በዚች አለም አንተን አፍቅሬያለዉ
እስከዛሬም አብሬህ ኖሬያለዉ
ደስ እንዲልህ ለአንተ ምን ያልሆንኩት አለኝ
እስቲ ይሄ ቀረሽ በለኝ
እኔ ላስደስት ስደክም ስለፋ ስደክም ስለፋ
ፊት ሲጨላልም ፈገግታ ሲጠፋ
ክፉ ባልናገር አንገቴን ብደፋ
ሁሉን ይችላል ወይ ሆድ ከሀገር ቢሰፋ
አንተ ላትደሰት ኩርፊያህን ላልገፋ ኩርፊያህን ላልገፋ
እኔ ስጨናነቅ ዉስጤን እየከፋዉ
በትካዜ መፍዘዝ ህመሜ እየፀና
ሀዘን በረታንኝ እንደምን ልፅና
ና ደባብሰዉ ጎኔን
ና ደባብሰዉ ጎኔን
ደስ እንዲለኝ እኔን
ተዉ ደባብሰዉ ጎኔን
ተዉ ደባብሰዉ ጎኔን
ደስ እንዲለኝ እኔን
ና ደባብሰዉ ጎኔን
ና ደባብሰዉ ጎኔን
ደስ እንዲለኝ እኔን
ተዉ ደባብሰዉ ጎኔን
ተዉ ደባብሰዉ ጎኔን
ደስ እንዲለኝ እኔን
በዚች አለም አንተን አፍቅሬያለዉ
እስከዛሬም አብሬህ ኖሬያለዉ
ደስ እንዲልህ ለአንተ ምን ያልሆንኩት አለኝ
እስቲ ይሄ ቀረሽ በለኝ
በዚች አለም አንተን አፍቅሬያለዉ
እስከዛሬም አብሬህ ኖሬያለዉ
ደስ እንዲልህ ለአንተ ምን ያልሆንኩት አለኝ
እስቲ ይሄ ቀረሽ በለኝ
በነጋ በጠባ ፊትህን እያየሁ ፊትህን እያየሁ
ጭንቀቴ በረታ እኔስ ተሰቃየሁ
የሌለህ አመል ያልፈጠረብህን
ለፍቅራችን ስትል ጨዋ መሆንህ
ስቀህ ስትጫወት የማገኘዉ ደስታ የማገኘዉ ደስታ
ተረት ሆኖ እንዳይቀር የማታ የማታ
እስኪ እንነጋገር ፊት ለፊት እናዉራ
ነገርን ሸፋፍነን ወደ ቂም አናምራ
ና ደባብሰዉ ጎኔን
ና ደባብሰዉ ጎኔን
ደስ እንዲለኝ እኔን
ተዉ ደባብሰዉ ጎኔን
ተዉ ደባብሰዉ ጎኔን
ደስ እንዲለኝ እኔን
ና ደባብሰዉ ጎኔን
ና ደባብሰዉ ጎኔን
ደስ እንዲለኝ እኔን
ተዉ ደባብሰዉ ጎኔን
ተዉ ደባብሰዉ ጎኔን
ደስ እንዲለኝ እኔን
ና ደባብሰዉ ጎኔን
ና ደባብሰዉ ጎኔን
ደስ እንዲለኝ እኔን
ተዉ ደባብሰዉ ጎኔን
ተዉ ደባብሰዉ ጎኔን
ደስ እንዲለኝ እኔን
ና ደባብሰዉ ጎኔን
ና ደባብሰዉ ጎኔን
ደስ እንዲለኝ እኔን
ተዉ ደባብሰዉ ጎኔን
ተዉ ደባብሰዉ ጎኔን
ደስ እንዲለኝ እኔን
ና ደባብሰዉ ጎኔን
ና ደባብሰዉ ጎኔን
ደስ እንዲለኝ እኔን
ተዉ ደባብሰዉ ጎኔን
ተዉ ደባብሰዉ ጎኔን
ደስ እንዲለኝ እኔን



Credits
Writer(s): Moges Teka
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link