Deha Nat

ጥሮ አዳሪ ለፍቶ አዳሪ
የእግዜር ደሀ ደክሞ ኗሪ
ደግ እሩሩህ ልበ ቀና
በሰው ኑሮ የማትቀና
እንደልፋቷስ ማን በለጣት
እድሏ ነው የሚያስቀጣት

ተዋት እሷን ተዋት ተዋት ለኔው ተዋት
ምስኪን ደሀ ናት
ተዋት እሷን ተዋት ተዋት ለኔው ተዋት
ደክሞ ኗሪ ናት

አስተዋይ እና አርቆ አሳቢ
ዘመድ አዝማድን ሰብሳቢ
አስተማሪ ሁሉን አዋቂ
መካሪ ናት አስታራቂ
አዛኝ ሰው ናት የምትሳሳ
ክፉ ደጉን የማትረሳ

ደሀ የኔ ደሀ
ደሀ የኔ ደሀ
ከርታታ ጨዋ
ተዋት ለኔው ተዋት ተዋት እሷን ተዋት
ደክሞ ኗሪ ናት

ተርፎ ባይተርፋትም አውቃለው ደሀ ናት
አታንስም ለራሷ የጤናም ሀብታም ናት
ሁሉን መስሎ ኗሪ ፀባይዋ ጉልበቷ
ደስታዋ ስራ ነው ጎጆዋ ኩራቷ
አሀሀ የማትገዛ አሀሀ ለብልጭልጩ
አሀሀ የድሀ ጎበዝ አሀሀ የኩራት ምንጩ
አሀሀ የማትደለል አሀሀ ባልረባ ነገር
አሀሀ እጇን የማትሰጥ አሀሀ የማትበግር

የኔ ጎበዝ የኔ ደሀ
ፍቅሯ 'ማይደርቅ የምንጭ ውሀ
ሀብታም በብር ቢያቅናጣም
ደሀ እንዳቅሙ ፍቅር አያጣም
ጥረው ግረው ያገኙት
ይጣፍጣል ሲበሉት
ቆሎም ሽሮም ጮማ ናቸው
ሰው ተፋቅሮ ከበላቸው

አቻም የለሽ ሰው ይላታል
ለመጠርያ ስም ያንሳታል
ቢደላትም ባይደላትም
የሚያውቅላት ሰው የላትም
እዘኑላት እባካችሁ
ደሀ አክባሪ የሆናችሁ

ተዋት እሷን ተዋት ተዋት ለኔው ተዋት
ደክሞ አዳሪ ናት
ተዋት እሷን ተዋት ተዋት እሷን ተዋት
ለፍቶ ኗሪ ናት
ላንድ እራሷ አንሳ አታውቅም
ትደክማለች እረፍት የላትም
ካላት ከፍላ ኑ ጉረሱ
የምትል ናት ተቃመሱ
ሀብቷ ጌጧ ድህነቷ
ፈጣሪዋ ነው ጉልበቷ
ተዋት እሷን ተዋት ተዋት ለኔው ተዋት
ደክሞ አዳሪ ናት
ደሀ የኔ ደሀ
ደሀ የኔ ደሀ
ከርታታ ጨዋ

ስጦታዋ እውነት በረከቷ ምክር
አምኖ ለተጠጋት ፍቅር የምታበድር
ከሷ ጋራ ኑሮ ለኔ ተስማምቶኛል
ጠግቤ ባላድርም ሰላሜ ተርፎኛል

አሀሀ የማትገዛ አሀሀ ለብልጭልጩ
አሀሀ የድሀ ጎበዝ አሀሀ የኩራት ምንጩ
አሀሀ የማትደለል አሀሀ ባልረባ ነገር
አሀሀ እጇን የማትስጥ አሀሀ የማትበግር

የኔ ጎበዝ የኔ ደሀ
ፍቅሯ 'ማይደርቅ የምንጭ ውሀ
ሀብታም በብር ቢያቅናጣም
ደሀ እንዳቅሙ ፍቅር አያጣም
ጥረው ግረው ያገኙት
ይጣፍጣል ሲበሉት
ቆሎም ሽሮም ጮማ ናቸው
ሰው ተፋቅሮ ከበላቸው
አይ አይ
ኡሁሁሁ
አቤት አቤት



Credits
Writer(s): Neway Debebe
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link