Amen

አሜን አሜን አሜን ልበል አስት አሜን
አሜን አሜን አሜን
አምላክ ፍቅሬን አንቺን ቢሰጠኝ አልኩ አሜን
አሜን አሜን አሜን አስት ልበል አሜን
አሜን አሜን አሜን
ሰላምን ጽናትን ፍቅርን ባንቺ አየሁ ህይወትን
ክፉ አይንካሽ በምድርርር ክፉ አይንካሽ በአለም
ኑርልኝ ዘላለም ዘላለም

አንቺ የህመሜ ሀኪም
አንቺ በጭንቅ የፈተንኩሽ
አንቺ ክፉ ቀን መወጫ
አንቺ ጉልበቴ ያረኩሽ
መጽናኛዬ ያልኩሽ
እህህ ብዬ እህህህህ ብዬ
እህህህህ ብዬ የልቤን ልንገርሽ

አንቺ የሂወት ምስክር
አንቺ የሄዋን ጉልበታም
አንቺ አንቺ አንቺ የእናቴ እህት ምትክ
አንቺ የደግነት ሃብታም
ነሽ ምግባረ መልካም
በደስታሽ በሳቅሽ ረካለሁ
ሲከፋሽ ስታዝኝም አዝናለሁ
ፍቅርን ህይወትን አስተምረሺኛል
አመሰግናለው ውለታሽ ከብዶኛል

አሜን አሜን አሜን ልበል አስት አሜን
አሜን አሜን አሜን
አምላክ ፍቅሬን አንቺን ቢሰጠኝ አልኩ አሜን
አሜን አሜን አሜን አስት ልበል አሜን
አሜን አሜን አሜን
ሰላምን ጽናትን ፍቅርን ባንቺ አየሁ ህይወትን
ክፉ አይንካሽ በምድርርር ክፉ አይንካሽ በአለም
ኑርልኝ ዘላለም ዘላለም

አንቺ የአስተዳደግ ውጤት
አንቺ የትዳር ጌጥ ዋልታ
አንቺ የትግስት ባለቤት
አንቺ የጨዋነት ጌታ
የፀጋ ገበታ
እህህ ብዬ እህህህህ ብዬ
እህህህህ ብዬ የልቤን ልንገርሽ

አንቺ የዳኝነት ሚዛን
አንቺ የሴት ሊቅ አስተዋይ
አንቺ አንቺ አንቺ የምስጢሬ ሙዳይ
አንቺ የጭንቅ ተካፋይ አርቀሽ አስተዋይ
በደስታሽ በሳቅሽ ረካለው
ሲከፋሽ ስታዝኝም አዝናለሁ
ፍቅርን ህይወትን አስተምረሺኛል
አመሰግናለው ውለታሽ ከብዶኛል



Credits
Writer(s): Neway Debebe
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link