Mela Atahu

አጥቻለው እኔስ እፎይታ
ያቅበጠብጠኛል ጠዋት ማታ
ስጠይቅ ፍቅር ነው ይሉኛል
መላ አጣሁ እንዴት ይሻለኛል
አጥቻለው እኔስ እፎይታ
ያቅበጠብጠኛል ጠዋት ማታ
በድንገት ፍቅር ደርሶብኛል
መላ አጣሁ እንዴት ይሻለኛል

ከሩቅ ከባሻገር አይሰጥ ምልክት
ከቶ እንዴት ይቻላል ፍቅርን መለየት
ቅድሞ ነጋሪቱን አይጎሽም አይመታ
ድንገት ከተፍ ይላል ሳያሰማ እእምቢልታ

ክተት ብሎ አይጀምር አውጆ አይነሳ
አይጣል ፍቅር ድንገት ሲነሳ
ደናውን ህሊና ከቦ በድንገት
አጥለቅልቆት ያድራል በሀሳብ በናፍቆት
ክተት ብሎ አይጀምር አውጆ አይነሳ
አይጣል ፍቅር ድንገት ሲነሳ
ደናውን ህሊና ከቦ በድንገት
አጥለቅልቆት ያድራል በሀሳብ በናፍቆት

አጥቻለው እኔስ እፎይታ
ያቅበጠብጠኛል ጠዋት ማታ
በድንገት ፍቅር ደርሶብኛል
መላ አጣሁ እንዴት ይሻለኛል
አጥቻለው እኔስ እፎይታ
ያቅበጠብጠኛል ጠዋት ማታ
በድንገት ፍቅር ደርሶብኛል
መላ አጣሁ እንዴት ይሻለኛል

መውደድን አዝምቶ ግንባር ቀደሙን
ልብን ይማርካል ሳይገብር ደሙን
ሀሳብ ፈጥኖ ደራሽ ደጀኑ ትዝታ
ወራሪው ፍቅር ድንገት የሚረታ

ማይጨው አልዘመተ አልዋለ ሰገሌ
እንዴት ይላል ደሞ ገሌሌ
አይፎክር አይሸልል ዘራፍም አያውቀው
ሀሳብ ብቻ ነው ወይ ፍቅር የታጠቀው
ማይጨው አልዘመተ አልዋለ ሰገሌ
እንዴት ይላል ደሞ ገሌሌ
አይፎክር አይሸልል ዘራፍም አያውቀው
ሀሳብ ብቻ ነው ወይ ፍቅር የታጠቀው



Credits
Writer(s): Hamelmal Abate
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link