God's Judgment (feat. Abenezer Dejene & Yafet Tesfaye)

ንጉሱ በግርማው ተቀምጧል
በፅድቁ ዙፈን ፊት ማንስ ይቆማል
ብርሃነትን እንደሸማ ተላብሷል ሁሉ በፊቱ አይጠላም ከቶ
አድርጎው ትክክል እውነተኛ ማነው አማካሪው ብቸኛ ዳኛ
የፍጥረትን ሩጫ በቃሎ ያበሰረ አእላፍ ከዋክብትን በእጁ የሰፈረ

ኦ ...

በእቢልታ በመለኮት ከአጥናፍ ድምፅ
ይሰማ ይዘመር እግዚአብሔር ሲነግስ
ከብዙ ውሆች ድምፅ ከባህር ሞገድ
የእግዚአብሔር ኃይል በእጥፍ ይልቅ
አልፍና ኦሜጋ ዘላለማዊ
አሃዱ ቀዳማይ የለው ተከታዩ
ብቻውን የገዛ ከዝንት ዓለም በፊት
አሁን'በመንበሩ አለ በሰማይ

ኦ...

የምድር ሀያላን ግዙፍ ተራሮች
የጥልቁ ነገስታት ጌታ ነኝ ባዮች
ኀጥኡን ሊሸሽጉት አልቻሉም
የእግዚአብሔር ጽዋ ሞልታለች አሁን
በልጁ ላመነ ለተቀበለው ግን
ማምለጥ ሆኖላታል ስለ ተሰቀለ
ማህተቡን ሊፈታ የተቻለው
ክብር ይሁን ምስጋና ለታረደው በግ

ኦ...

መልስ አለ ገና ለተናቀ ለተገፋው
እንዲሁ አያልፍም እንዳመረረ እንደ ከፋው
ፍትህ ይወርዳል ከላይ ሳይዛባም ፍርዱ
ላንዱ ሊያበቃ ስቃይ ላንዱ ግን ነው ጉዱ
የሌለው ግራና ቀኝ አማካሪ ብቸኛ
አይደለም ፍርደ ገምድር ሁሌም ነው እውነተኛ
አልፋ እና ኦሜጋ ፊተኛውና ኋለኛ
ሁሉም ሰገደ ለክብሩ ማን ችሎ ሊቆም በፊቱ

ደግ አባት ለሁሉም ሚራራ
ለፍጥረቱ ፀሐይ የሚያበራ
ለጻድቅ በክፉ ሳይሰስት ሁሉን
የሚጎበኝ ለሁሉ የሚያዘንብ
ታማኝ ወዳጅ እጅግ ታጋሽአዛኝ አፅናኝ ብርቱ ፈዋሽ ምህረትን የተሞላ ለታመኑት ፈጥኖ ደራሽ

የለማ አማራጭ
እኩያ በጭራሽ
ነፍሴ ተጠማች
መገኘትህንም ናፈቀች

ድንቅ አምላክ ቸር መካር
የሆነ የሰላም አለቃ ከልቤ ሲገባ
ጭንቀት ስጋቴ አበቃ
ኢየሱስ



Credits
Writer(s): Abenezer Tulu
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link