Endegena

አብዝቼም ቻልከኝ አልሰለቸህም
ትግስትህን ያሟጠጥኩኝ መስሎኝ ለካ ልክ የለውም
ተስፋ መቁረጤ አላስቆመህም ከፍቅር አላማ
ስሰባበር ስትጠግን አለቀ ስል ስትጀምር
ምስጋና ለፀጋህ ክብር

እንደገና ረዳሄኝ
እንደገና አቆምከኝ
እንደገና ራራሄኝ
እንደገና አቆምከኝ
እንደገና እንደገና

የማይመጥነኝ ቦታ ፈቅጄ ሲገኝ
ፍቅርህን ካልቀመሱት ጋራ ያሸኝን ሲሆን
የአዋቂ አጥፊ ደሜን አግፋፊ ብለህ አልተውኝ
እየገፋሁ ትቀርበኛለህ በደሌን መቼ ትቆጥራለህ
ያለ ልክ ትዎደኛለህ

እንደገና ረዳሄኝ
እንደገና አቆምከኝ
እንደገና ራራልኝ
እንደገና አቆምከኝ
እንደገና እንደገና

(እንድገና)
እንደገና እንደገና



Credits
Writer(s): Illasha Tessema
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link