LEQSO(ZIKRE EYOB)

ያለ ፀሀይ በትካዜ ወጣሁኝ ያን ተራራ
ለቀበሮ ወንድም ሆኜ ለሰጎንም ባልንጀራ
ቁርበቴ ጠቁሮ ከኔም ላይ ወደቀ
አጥንቴም በለሊት በደዌ ደቀቀ

ምሬት ሞልቶብኝ በእሬትም ጠገብኩኝ
ነፍሴ ከሰላም ስትርቅ በጎነትን እረሳሁኝ
ማሲንቆዬ ለሃዘን ሲሆን እምቢልታዬም ለቅሶ
ወገኖቼም ቁስሌን ከበው ሰደዱብኝ እሾህ

ነፍሴ አምላኳን ስታስብ ፈዘዘች
ከጠላትም ሰይፍ እንድትድን ለመነች
በመከራዬ ቀን ጩኸቴን ይሰማል
አለች ጠበቃለሁ አንድ ቀን ይመጣል

ለአመፃና ክፉ እጅ አሳልፈኽ ብትሰጠኝ
በእቶን ውስጥ ስከተት ፈጥነህ ባታድነኝ
እንደጊደር እና ላም እንደሰባም በግ
በእሳቱ ውስጥም ስነድ ልሁን መስዋት

ነፍሴ አምላኳን ስታስብ ፈዘዘች
ከጠላትም ሰይፍ እንድትድን ለመነች
በመከራዬ ቀን ጩኸቴን ይሰማል
አለች ጠበቃለሁ አንድ ቀን ይመጣል

እርሱ ካሸከመኝ በጫንቃዬ ቀንበር
በዝምታ ልቀመጥ አፌን አፈር ውስጥ ልቅበር
ስጋዬን በጥርሴ ይዤ ላኑር ህይወቴን በጄ
ቢገድለኝ እንኳ ልጠብቀው እርሱኑ ታግሼ



Credits
Writer(s): Dawit Cherent
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link