HELM

ሁለት ወደኋላ አንድ ተራምዶ
እምሄድ መስዬ እያየው ማዶ
አደናቀፈኝ ያላየሁት ነዶ
ህልሙም ጠፋ ያየሁት ድሮ

ለውጬው ይሆናል ሲሸጡኝ ያኔ
ሲቸግረኝ ገንዘብ እና እድሜ
ይዜ ያልያዝኩኝ መሰለኝ
ብዙ ደራርቤ በረደኝ

እቤቱ እሩቅ ነው የህልመኛው ተስፋ
ግን መናኝ ተጏዥ በሀገሩ ባዳ
እግር ይዞ አይሻገርም ወንዝ
ትንሽ ቢያሸልብ የሚያየው ቅዠት

እሩቅ ወስዶኝ ጌታው አደረኝ ባሪያው
ህልሜ ውስጥ የሌለን አየሁኝ በእውኔ
የነፃነትም ድምፅ ሲያውቁ እንደጠፋኝ
ቁልፍ አሲዘውኝ ታሰርኩ ሆኜላቸው ታማኝ

ህልም አለኝ ቢሉ ፈታሁላቸው
እነርሱ ያላዩትን እኔ አየሁላቸው
ምን አልባት ህልም መንገዱ ይሄ ነው
በወንድሞች መሸጥ አላየንም ብለው

እቤቱ እሩቅ ነው የህልመኛው ተስፋ
ግን መናኝ ተጏዥ በሀገሩ ባዳ
እግር ይዞ አይሻገርም ወንዝ
ትንሽ ቢያሸልብ የሚያየው ቅዠት

እቤቱ እሩቅ ነው የህልመኛው ተስፋ
ግን መናኝ ተጏዥ በሀገሩ ባዳ
እግር ይዞ አይሻገርም ወንዝ
ትንሽ ቢያሸልብ የሚያየው ቅዠት



Credits
Writer(s): Dawit Cherent
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link