Meleyet Kifu Eta

ተስለሻል እንዴ?
ካይኔ ከመሃሉ
አንቺ ብቻኮ ነሽ
በሚታየኝ ሁሉ

ተስለሻል እንዴ?
ካይኔ ከመሃሉ
አንቺ ብቻኮ ነሽ
በሚታየኝ ሁሉ
አንቺ ብቻኮ ነሽ
በሚታየኝ ሁሉ

የዳመናውን ጭስ ወደላይ አይኔ ተከትሎ
የዳመናውን ጭስ ወደላይ አይኔ ተከትሎ
ባሳቡ ያይሻል ከባዶ ላይ ስሎ
ከባዶ ላይ ስሎ
የሚጣፍጥ ህመም ስሜት ነው
ቅር የሚል ደስታ
የሚጣፍጥ ህመም ስሜት ነው
ቅር የሚል ደስታ
ሙሉ ጎዶሎ ነው ትርጉሙ ትዝታ
ትርጉሙ ትዝታ

ከኔ አንጀት ይመስል ይገርማል የተሰራው ክሩ
ከኔ አንጀት ይመስል ይገርማል የተሰራው ክሩ
ይረበሻል ሆዴ ሲገረፍ ክራሩ
ሲገረፍ ክራሩ

አይታይሽም ወይ የኔ አበባ የልቤ ውስጥ እሳት
ስንቱን አሳለፍኩት የኔ አለም አንቺን ላለመርሳት
ሳድር ለብቻዬ የኔ አበባ ስወድቅ ስነሳ
አስታውስሻለሁ የኔ አለም እኔ አንቺን አልረሳም

ሰማይ ደም ቢመስል
ብጠቁርም ጨረቃ
ሳላይሽ አላድርም
እኔ አልችልም በቃ
አልችልም በቃ
ደመናው ተቀዶ
ዶፍ ቢወርድ ከሰማይ
አልችልም ለማደር
አይኖችሽን ሳላይ
አንቺን ሳላይ

ምን ጉድ ነው መለየት ክፋቱ
ጨክኗል ተመዟል ካፎቱ
ሊለየን ሊያርቀን ቢነሳም
አይችልም እኔ አንቺን አልረሳም
ምን ጉድ ነው መለየት ክፋቱ
ጨክኗል ተመዟል ካፎቱ
ሊለየን ሊያርቀን ቢነሳም
አይችልም እኔ አንቺን አልረሳም

ተስለሻል እንዴ?
ካይኔ ከመሃሉ
አንቺ ብቻኮ ነሽ
በሚታየኝ ሁሉ

ተስለሻል እንዴ?
ካይኔ ከመሃሉ
አንቺ ብቻኮ ነሽ
በሚታየኝ ሁሉ
አንቺ ብቻኮ ነሽ
በሚታየኝ ሁሉ

ስንቱን ጋራ ዞረሽ የኔ አለም
ስንቱን ጋራ ዞሬ
ስንቱን ጋራ ዞረሽ የኔ አለም
ስንቱን ጋራ ዞሬ
እንዴት እንዳዲስ ሰው ታሚኛለሽ ዛሬ
ታሚኛለሽ ዛሬ
እስኪ ልጠይቀው ጥርስሽን
ምን ይሆን ምክንያቱ
እስኪ ልጠይቀው ጥርስሽን
ምን ይሆን ምክንያቱ
ፈገግ ብሎ ሸኘኝ ሲቆረጥ አንጀቱ
ሲቆረጥ አንጀቱ

ከኔ አንጀት ይመስል ይገርማል የተሰራው ክሩ
ከኔ አንጀት ይመስል ይገርማል የተሰራው ክሩ
ይረበሻል ሆዴ ሲገረፍ ክራሩ
ሲገረፍ ክራሩ

አይታይሽም ወይ የኔ አበባ የልቤ ውስጥ እሳት
ስንቱን አሳለፍኩት የኔ አለም አንቺን ላለመርሳት
ሳድር ለብቻዬ የኔ አበባ ስወድቅ ስነሳ
አስታውስሻለሁ የኔ አለም እኔ አንቺን አልረሳም

ሰማይ ደም ቢመስል
ብጠቁርም ጨረቃ
ሳላይሽ አላድርም
እኔ አልችልም በቃ
አልችልም በቃ
ደመናው ተቀዶ
ዶፍ ቢወርድ ከሰማይ
አልችልም ለማደር
አይኖችሽን ሳላይ
አንቺን ሳላይ

ምን ጉድ ነው መለየት ክፋቱ
ጨክኗል ተመዟል ካፎቱ
ሊለየን ሊያርቀን ቢነሳም
አይችልም እኔ አንቺን አልረሳም
ምን ጉድ ነው መለየት ክፋቱ
ጨክኗል ተመዟል ካፎቱ
ሊለየን ሊያርቀን ቢነሳም
አይችልም እኔ አንቺን አልረሳም



Credits
Writer(s): Elias Woldemariam, Eiyubel Birhanu, Nuredien Eisa
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link