Salaysh

ይመቸኛል ካንቺ ጋር ጨዋታ
አይጥመኝም እጠላለው ዝምታ
በይ አናግሪኝ አንደበትሽ ይልመድ
እንድንዋደድ

አንደኛዬ የልቤ መድረሻ
እንግዳዬ የፍቅሬ መነሻ
አልተውሽም እኔ እነግርሻለው
እወድሻለው
ሚስጥሬን ነግሬ ካልወጣልኝ
ማፍቀር ለብቻዬ ምን ሊረባኝ
ልናገረው እንጫወት
ካፈቀርኩሽ የምን ስስት

እስኪ ባንደበቴ ልናገረው
ሆዴ እንዲተነፍስ እንዲቀለው
ካሉኝ አይቀር፣አበደላት
የሱዋን ፍቅር፣ላውጅላት

የኔ የኔ የኔ ነሻ
ከቃል በላይ ጭንቄን መርሻ
ቀዳማዊት እመቤቴ
የግልሽ ነው ኑሪ ቤቴ
የኔ የኔ የኔ ነሻ
ከቃል በላይ ጭንቄን መርሻ
ቀዳማዊት እመቤቴ
የግልሽ ነው ግቢ ቤቴ

ይመቸኛል ካንቺ ጋር ጨዋታ
አይጥመኝም እጠላለው ዝምታ
በይ አናግሪኝ አንደበትሽ ይልመድ
እንድንዋደድ
አንደኛዬ የልቤ መድረሻ
እንግዳዬ የፍቅሬ መነሻ
አልተውሽም እኔ እነግርሻለው
እወድሻለው

ሙሉ አይደለምና ሰው በራሱ
የሚወደው አለው እንደ ነፍሱ
ካፍሽ ፍሬ ልብላ ከከንፈርሽ
አይንሽ ስር ቁጭ ብዬ ሁሌ እንዳይሽ
በዝች መንገድ ዓለም ልታርፊባት
በልብሽ እፎይን አትንፈጊያት
አንችን ደስ ብሎሽ ተሳክቶልኝ
እኔም በተራዬ ዝም ባልኩኝ

የኔ የኔ የኔ ነሻ
ከቃል በላይ ጭንቄን መርሻ
ቀዳማዊት እመቤቴ
የግልሽ ነው ግቢ ቤቴ
የኔ የኔ የኔ ነሻ
ከቃል በላይ ጭንቄን መርሻ
ቀዳማዊት እመቤቴ
የግልሽ ነው ግቢ ቤቴ

የኔ የኔ የኔ ነሻ
ከቃል በላይ ጭንቄን መርሻ
ቀዳማዊት እመቤቴ
የግልሽ ነው ግቢ ቤቴ

ኦሆሆ ላ ላ ላ ላ
ኦሆሆ ኦሆሆ ላ ላ ላ ላ
ኦሆሆ ላ ላ ላ ላ



Credits
Writer(s): Elias Woldemariam, Eiyubel Birhanu, Yilma G/ab
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link