Tsedal (Special Version)

ፀዳል

ያየሽ ይፍረደኝ ዛሬማ ያየሽ ይፍረደኝ
ውበትሽ ደምቆ በቁሜ ይዞ እያራደኝ
ካንቺው ጋር ነኝ ካንቺው ካንቺው ጋራ ነኝ
እንዳይለየኝ ካንቺማ እንዳይለየኝ

ደስታዬ ነሽ ለኔ
ምክንያት ለኩራቴ ፀዳል ውበቴ
ተስፋዬ ነሽ ለኔ
ህልምና መብራቴ ገላ ድምቀቴ

ስንት ዘመን ሁሉ ስጠብቅሽ ኖሬ
ወንድነቴ ራደ ሳየው የኛን ፍሬ
ቃልኪዳኔን ይዤ ወዳንቺ ስመጣ
አሜን አሜን አልኩኝ ሲያረግሽ የኔ እጣ

ደስታዬ ነሽ ለኔ
ምክንያት ለኩራቴ ፀዳል ውበቴ
ተስፋዬ ነሽ ለኔ
ህልምና መብራቴ ገላ ድምቀቴ

አንቺን በጄ ይዤ ከደጃፉ ስደርስ
ማን ይገዳደረው የኔን ግርማ ሞገስ
ቸብ ቸብ ሲያደርጉት የከበቡን ሁላ
ፊቴ ላይ ዘነበ ደስታዬ እየሞላ

ደስታዬ ነሽ ለኔ
ምክንያት ለኩራቴ ፀዳል ውበቴ
ተስፋዬ ነሽ ለኔ
ህልምና መብራቴ ገላ ድምቀቴ

ሰው መቼስ ይታደላል
ከማማው ላይ ይውላል
ንጉስ ነኝ ለዛሬው ቀን
ሽር እንበልባት ደምቀን
ይችትና ምወዳት
አጅቧት ንግስቴ ናት
ቤቱን ደመቀችበት
እሷም አወቀችበት
ቸብ ቸብ አድርጉላት አንድ እኮ ናት ለናቷ
ቸብ ቸብ አድርጉላት አንድ እኮ ናት ላባቷ
ለተሰጣት ተፈጥሮ ለልዩ ሴትነቷ
ቸብ ቸብ አድርጉላት ለንፁህ አፍቃሪነቷ

ደስታዬ ነሽ ለኔ
ምክንያት ለኩራቴ ፀዳል ውበቴ
ተስፋዬ ነሽ ለኔ
ህልምና መብራቴ ገላ ድምቀቴ



Credits
Writer(s): Samuel Alemu, Sami Dan
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link