Birr Indaygezash (Live)

ደስታ በሞላት በትንሽዋ ቤቴ
የምኖር ሰው ነኝ ከነ ነፃነቴ
ምንም ቢሸፈን ቆሽሾ ውበቴ
አለ ግን ከፊቴ
አንቺ አይተሽው ያደፈውን ልብሴን
ገምተሽ ኖሮ የኔ ማንነቴን
ነውር አርገሽው አንቺ ሰው መውደዴን
አሳቀቅሽው ልቤን
ልንገርሽ ትልቅ ስህተትሽን
መች አየሽ እኔን አፍቃሪሽን
ሰላሜን፣ እምነቴን፣ ፅናቴን ውበቴን እውቀቴን
አርገሽው መሽቀርቀርን ችሎታ
ባስብሽ አለፍሽኝ በቸልታ
መች ገባሽ፣ ሰው መሆን፣ ትርጉሙ ሚስጥሩ ታምሩ
አትይ የልብሴን ጨርቅ
ቢቆሽሽም ሸፍኑዋል እኔን መሳይ ወርቅ
የምታይው አብለጭላጩ
ከላይ እንጂ ውስጡ ባዶ ውሸት ነው ምንጩ

ብትሄጂም ግድ የለኝ ብቻ እወቂ
ብር እንዳይገዛሽ ተጠንቀቂ
የሰው ልጅ ማረፊያው ፍቅር ካልሆነ
ኃላ ይገለዋል ብቸኝነት እያደነ
ብትሄጂም ግድ የለኝ ብቻ እወቂ

ብር እንዳይገዛሽ

የምታይው ሁሉ ትልቅ የሚመስለው
የሚንኮታኮት መሰረት የሌለው
ህሊናን ሸጦ ስሙን ሲገነባው
መች በራሱ አመጣው
ትዕቢት ወጥሮት ያለኔ ማነው ባይ
በያረፈበት የሌለው ገላጋይ
በደሃ ህዝቦች ሲከበር ስታይ
ችሎ ወድቀሻል እጁ ላይ
ቢሆንም በትንሽ ቤት ምኖረው
ልቤ ግን ሀገር ነው ሚያክለው
ሰላሜ፣ እምነቴ፣ ፅናቴ ውበቴ እውቀቴ
ሳልደብቅ ፍፁም ማንነቴን
ያየሽው ውሎና ኑሮዬን
ይኸው ነው፣ ሰው መሆን፣ ትርጉሙ ሚስጥሩ ታምሩ
የልቤ ንፅህና ልክ እንደ በረዶ ሆሆ እንደ ደመና
ከመጣሽ ግዛትሽ ነው ጥቁር ነጥብ እንኩዋን ፍፁም የሌለው
ብትሄጂም ግድ የለኝ ብቻ እወቂ
ብር እንዳይገዛሽ ተጠንቀቂ
የሰው ልጅ ማረፊያው ፍቅር ካልሆነ
ኃላ ይገለዋል ብቸኝነት እያደነ
ብትሄጂም ግድ የለኝ ብቻ እወቂ
ብር እንዳይገዛሽ



Credits
Writer(s): Getaneh Bitew
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link