Mengedu

መንገዱ

ከባርነት ቀንበር አርነት ስወጣ
ነፃነቴን ሳገኝ ከግዞት ስፈታ
መቼ ፍቃድ ሰጠኝ ለሀጥያት ይሁንታ
ዳግም ታስሬአለው ለፈታኝ በደስታ

ተነስቼ አልነጉድም መሪ እንዳጣ መንጋ
አቅጣጫዬን አልስት ቀያሹ ቢበዛ
መንገዱ እራሱ ክርስቶስ ነውና
ዘላለም ነው ማብቂያው የጉዞው መድረሻ

አልሆንም እንዳሻኝ እንደልቡ ኗሪ
እንደዕንግዳ እኖራለሁ እንዳለበት ጥሪ
እንዳልደላደል ተመችቶኝ ጤዛ በሆነች ጠፊ ድንኳን
ቃሉ መርሄ ነው ኑሮዬን እንድቃኝ

ተነስቼ አልነጉድም መሪ እንዳጣ መንጋ
አቅጣጫዬን አልስት ቀያሹ ቢበዛ
መንገዱ እራሱ ክርስቶስ ነውና
ዘላለም ነው ማብቂያው የጉዞው መድረሻ

ተነስቼ አልነጉድም መሪ እንዳጣ መንጋ
አቅጣጫዬን አልስት ቀያሹ ቢበዛ
መንገዱ እራሱ ክርስቶስ ነውና
ዘላለም ነው ማብቂያው የጉዞው መድረሻ



Credits
Writer(s): Tsega Abebe
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link