Like the Sun Shines on Meadows

ፀሀይ ለሁሉም እንደምታበራ
ሜዳ ገደል ሳትል እንደምትበራ
ጌታየ ብርሀንህ ይብራ
እረፍት የሚሆን ችቦ በራ

የትንሳኤ ብርሀን ጮራ
በሁሉም ዘንድ ይብራ
አማኝ ሲደሰት ሳር ቅጠሉ
አትርሳ ያለውን በመከራ

ፀሀይ ለሁሉም እንደምታበራ
ሜዳ ገደል ሳትል እንደምትበራ
ጌታየ ብርሀንህ ይብራ
እረፍት የሚሆን ችቦ በራ

ዛሬ ከዘላለም ሞት
የዳንባት ታላቅ እለት
ሞቴ ድል ሆነ በምህረትህ
ይፈር፣ ሞት ይፈር በሞትህ

ፀሀይ ለሁሉም እንደምታበራ
ሜዳ ገደል ሳትል እንደምትበራ
ጌታየ ብርሀንህ ይብራ
እረፍት የሚሆን ችቦ በራ

እንዘምር በአንድነት
ለሰጠን የዘላለም ህይወት
ሁሉም ይመራ በእውነት
ካገኘ የአምላክ ልጅነት

ፀሀይ ለሁሉም እንደምታበራ
ሜዳ ገደል ሳትል እንደምትበራ
ጌታየ ብርሀንህ ይብራ
እረፍት የሚሆን ችቦ በራ

የፍቅር በትር የተዋበች ናት
ፍቅር፣ ሰላም፣ አንድነት ያላት
ሁሉም አበባ የሞሏት
የተለያዩ ዕጽዋት

ፀሀይ ለሁሉም እንደምታበራ
ሜዳ ገደል ሳትል እንደምትበራ
ጌታየ ብርሀንህ ይብራ
እረፍት የሚሆን ችቦ በራ

ነች ማርያም ሕይወት
ድንግል ማርያም ዕፀ መድኃኒት
አንች የተገኘው ኅብስተ ሕይወት
ሞትን ሻረ በድል አድራጊነት

ፀሀይ ለሁሉም እንደምታበራ
ሜዳ ገደል ሳትል እንደምትበራ
ጌታየ ብርሀንህ ይብራ
እረፍት የሚሆን ችቦ በራ

በርሱ ሞት ያገኘናት
እየሩሳሌም ሰማያዊት
ተስፋ የጻድቃን፣ የሰማእት
ተሰጠችን በትንሳኤ እለት

ፀሀይ ለሁሉም እንደምታበራ
ሜዳ ገደል ሳትል እንደምትበራ
ጌታየ ብርሀንህ ይብራ
እረፍት የሚሆን ችቦ በራ



Credits
Writer(s): Emahoy Tsege Mariam Gebru
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link