Tizita

አግኝቶ ላያገኝ ወይ ጠቅሞ ላይጠቅመዉ
ሰው ለምን ይኖራል ትዝታ ሲያደክመዉ(2×)
ትርጉሙ ምንድነው ምንድነው ትዝታ
ምንድነው ሰው ማሰብ ምንድነው ትዝታ
ባክህ ተዉ የማይሉት የሁሉም ሰዉ ጌታ
ይሃዉ ሰው ይኖራል በትዝታ ሰበብ(2×)
የሃሊት ሲጋልብ ትናንት በማሰብ
ሰው እንዴት ባለፈው በትናንት ይኖራል(2×)
ዛሬን በእጁ ይዞ ለነገው መሰላል(2×)
እልል በል ትዝታ ልርሳ በሽታዬን
አትጋርደኝ ልይበት የነገን ተስፋዬን
ባይጠፋ አሻራው ትዝታ ቢነፍስም
ባለፈ አመት ዝናብ ዛሬ አይታረስም
በትዝታ ሰበብ ላለፈው ሲጨነቅ
ስንት ሰው አለፈ ከአምላክ ሳይታረቅ
እገነባለሁ ብዬ ድካሙ ቢያመኝም
ለፈረሰዉ ቤቴ ሳለቅስ አልገኝም
ያለፈን ላይቀይር በከንቱ ይለፋል(2×)
መቼም ሰው ደፋር ነው ፈጣሪን ይጋፋል
ትንሽ እልፍ ሲሉ እልፍ እየተገኘ(2×)
ድሀ ነው በልቡ ሞትን የተመኘ
ለምን በትዝታ ኑሮዬን እገፋለሁ(3×)
ማጣትም እንዳለ ለማግኘት ጊዜ አለዉ(2×)
አቅም አለኝ ብሎ የሰው ልጅ ቢሰፍርም (3×)
ታሰበ አልታሰበ ከልኩ አያልፍም(6×)
አግኝቶ ላያገኝ ወይ ጠቅሞ ላይጠቅመዉ
ሰው ለምን ይኖራል ትዝታ ሲያደክመዉ(2×)



Credits
Writer(s): Elias Woldemariam, Tesfa Birhan
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link