Lidjenet Alat

ልቤ መሸነፉን እንዳይነግራት ሰጋ
ወራቱም አለፈ ክረምትና በጋ
የሆዴን መጨነቅ ፍቅሬ መች ገባት
ትስቃለች እሷ ልጅነት ይዟት

ልቤ መሸነፉን እንዳይነግራት ሰጋ
ወራቱም አለፈ ክረምትና በጋ
የሆዴን መጨነቅ ፍቅሬ መች ገባት
ትስቃለች እሷ ልጅነት ይዟት

በውበት ቁንጅና መልኳ መች አነሰ
ቀርቤ እንዳልነግራት ልጅነቷ ባሰ
የሆዴ መጨነቅ ባይገባት ነው ለሷ
ቀርቤ ስነግራት የሚስቀው ጥርሷ

ልቤ መሸነፉን እንዳይነግራት ሰጋ
ወራቱም አለፈ ክረምትና በጋ
የሆዴ መጨነቅ ፍቅሬ መች ገባት
ትስቃለች እሷ ልጅነት ይዟት

ተይ አስታሚው መራቅሽ ይቅር
ግፍ አትስሪ ጡር አለው ፍቅር
እንደሰት ልርሳሽ ከሆዴ አውጥቼ
ባይንሽ ውበት እዳ ገብቼ
እዳ ገብቼ እዳ ገብቼ
አስረሽኛል አልሠዎስም
እስቲ ፍቺኝ በይ እንደ ቄስ
እንዳልከስሽ ለመሪ፟ጌታ
ከልጅ ውሎ የለም ስሞታ
የለም ስሞታ የለም ስሞታ

ልቤ መሸነፉን እንዳይነግራት ሰጋ
ወራቱም አለፈ ክረምትና በጋ
የሆዴን መጨነቅ ፍቅሬ መች ገባት
ትስቃለች እሷ ልጅነት ይዟት

ልቤ መሸነፉን እንዳይነገሸራት ሰጋ
ወራቱም አለፈ ክረምትና በጋ
የሆዴን መጨነቅ ፍቅሬ መች ገባት
ትስቃለች እሷ ልጅነት ይዟት

ልነግራት እልና ነገ ዛሬ እያልኩኝ
የፍቅርን እረመጥ አዝዬው ከረምኩኝ
ሆዴ ላይሆንለት እንዲያው ተጨነቀ
ሁኔታዋ ሁሉ ነብስ እንዳላዎቀ

ልቤ መሸነፉን እንዳይነግራት ሰጋ
ወራቱም አለፈ ክረምትና በጋ
የሆዴን መጨነቅ ፍቅሬ መች ገባት
ትስቃለች እሷ ልጅነት ይዟት

አሳምሮ ውበት ቢያድላት
ፍቅር አታውቅም ልጅነት አላት
ተመኝቼው ድንቅ ውበቷን
እንዴት ላርገው ልጅነቷን
ልጅነቷን ልጅነቷን

ቀድማ ስቃ ቀልቤን ገዛችው
ልቤን ማርካ ደጅ አስጠናችው
ወይ አትደግፈኝ አዝና ለነብሷ
ትስቃለች ተይዤ በሷ
ተይዤ በሷ ተይዤ በሷ

አሳምሮ ውበት ቢያድላት
ፍቅር አታውቅም ልጅነት አላት
ልጅነት አላት ልጅነት አላት
ተመኝቼው ድንቅ ውበቷን
እንዴት ላርገው ልጅነቷን
ልጅነቷን ልጅነቷን



Credits
Writer(s): Teddy Afro
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link