Alfa Neh Omega

ከማንም ጋር አላወዳድርም
ከማንም ጋር እኩያ አላረግህም
ከማንም ጋር አላወዳድርም
ከማንም ጋር እኩያ አላረግህም
ለጌታዎቹ ጌታ ነህ
ለነገስታቱ ንጉስ ነህ
ለኀያላኑ ኀያል ነህ
እግዚአብሔር ልዩ ነህ
ከዘላለም ዘላለም በፊት ብቻህን የነበርከው
ከዘላለም ዘላለም በኋላ ብቻህን የምትኖረው
ፍጥረት ቢያመልክ ባያመልክህ
ቢሰግድ ባይሰግድልህ
ከክብርህ ቅንጣት አይቀንስም እንኳንስ ሊያጎልብህ
ቅንጣት አይቀንስም እንኳንስ ሊያጎልብህ
ከክብርህ ቅንጣት አይቀንስም እንኳንስ ሊያጎልብህ
ቅንጣት አይቀንስም እንኳንስ ሊያጎልብህ

እውነት ነው እኔ ዝም ብል ድንጋዮች ይናገሩልሃል
እጅ እግሬን አጥፌ ብቀመጥ ኮረብቶች ይዘሉልሃል
ወንዞች ያጨበጭቡልሃል አዕዋፋት ይዘምሩልሃል
ስለጎደለህ አይደለም እኔ የምጨምረው
ስላነሰህም አይደለም እኔ የማበዛው
ስለሚገባህና ስለተገባህ ነው
ስለሚገባህና ስለተገባህ ነው

የተለየ ነው አምላክነት ንግስናህ
የተለየ ነው ገናናነት ዝናህ
የተለየ ነው መቀመጫ ዙፋንህ
የተለየ ነው ማስፈራቱ የክብርህ
አልፋ ነህ ዖሜጋ መጀመሪያ መጨረሻ (×፭)
ሁሉን የምትገዛ ጌታ



Credits
Writer(s): Samuel Bizuneh
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link