Siwur Esren

ገመድ በአንገቴ ሳይገባ
እጅም ሰንሰለት ሳያስረው
እግሬ እየዘለለ አየተወራጨሁ
ታዲያ የምን እስራት ነው
ታዲያ የምን እስራት ነው

ጌታ ሆይ ስውር እስሬን አሳየኝ
እንዳልራመድ ያደረገኝ አሳየኝ
ጌታ ሆይ ስውር እስሬን አሳየኝ
እንዳልራመድ ያደረገኝ አሳየኝ
ዓይኔ እያየ በሚያልፈው ላይ
እንዳልዘረጋ እጄን መዘዙን ሳላይ
እንድጋልብበት ሲያምረኝ ፈረሱ
ልጓም ከሌለው ይቅርብኝ እርሱ
ዓይኔ እያየ በሚያልፈው ላይ
እንዳልዘረጋ እጄን እባክህ እርዳኝ
እንድጋልብበት ሲያምረኝ ፈረሱ
ልጓም ከሌለው ይቅርብኝ እርሱ

ጌታ ሆይ ስውር እስሬን አሳየኝ
እንዳልራመድ ያደረገኝ አሳየኝ
ጌታ ሆይ(ኢየሱስ ሆይ) ስውር እስሬን አሳየኝ(አሳየኝ)
እንዳልራመድ ያደረገኝ አሳየኝ
ከንጉሥ ገበታ ከቃሉም ማዕድ
ሁሌም ማልጠፋ ሆኜ የንጉሥ ልጅ
ምነው መክሳቴ ምነው መመንመኔ
የዓለም ቤዛ ሆነኀኝ መድህኔ
ከንጉሥ ገበታ ከቃሉም ማዕድ
ሁሌም ማልጠፋ ሆኜ የንጉሥ ልጅ
ምነው መክሳቴ ምነው መመንመኔ
የዓለም ቤዛ ሆነኀኝ መድህኔ

ገመድ ከአንገቴ ሸክም ከጫንቃዬ
ይሰበር የእግር ብረቱ
ይቆረጥ ከእጄ ሰንሰለቱ

ፍታልኝ እባክህ ፍታልኝ
ፍታልኝ እስሬን ፍታልኝ
ፍታልኝ እባክህ ፍታልኝ
ፍታልኝ ውዴ ፍታልኝ
ፍታልኝ እባክህ ፍታልኝ
ፍታልኝ እስሬን ፍታልኝ
ፍታልኝ እባክህ ፍታልኝ
ፍታልኝ ውዴ ፍታልኝ

ፍታልኝ ፍታልኝ
ኢየሱስ እስሬን ፍታልኝ
አባቴ አባቴ ፍታልኝ
ፍታልኝ



Credits
Writer(s): Samuel Bizuneh
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link