Dosiew

እስኪ ዶሴዉ ይዉጣ የምጠየቅበት
ወንጀሌን ሳላዉቀዉ እኔ አልቀጣበት
እኔ አልቀጣበት
በማላዉቀዉ ጉዳይ ከመሰላት ዉላ
የተከሰስኩ እኔ የደፈራት ሌላ
የደፈራት ሌላ

እስኪ ዶሲዉ ይዉጣ የምጠየቅበት
ወንጀሌን ሳላዉቀዉ እኔ አልቀጣበት እኔ አልቀጣበት
በማላዉቀዉ ጉዳይ ከመሰላት ዉላ
የተከሰስኩ እኔ የደፈራት ሌላ
የደፈራት ሌላ

የሞላ ማድጋ አያዉቀዉም ሽንጧን
እኔም አልክደዉም ሙሉ መቆየቷን
ስወድሽ እንደሆን ሁሉም ስላወቀዉ
በግምት ብቻ ነዉ የምጠረጠረዉ

እይ አይ አሃሃሃይ
ልጥላ ወይ ልዉደድሽ ደግም አልዋልሽልኝ
ወዳጄ እንዳትባይ በጎ አላሰብሽልኝ
የድብቅ የድብቅ ድንገት ባደረግሽዉ
አስወነጀልሽኝ ወይ በኔ ላይ ላከክሽዉ

አምባሩን ያጌጠበት ሌላ
ተከሳሽ አምሮት ያጣ ገላ
አምባሩን ያጌጠበት ሌላ
ተከሳሽ አምሮት ያጣ ገላ

ምስክር አልጠራ ወንጀለኛ እንዳልሆን
ሆኗል ያሉት ነገር ሰዉ እያየን አይሆን
ጅምሩን ይጨርስ ቢሉም ቢፈርዱብኝ
እዳዉን አምኖ እንጂ ወዶ አገባ አይሉኝ

እይ አይ አሃሃሃይ
እንዳጎደልሽብኝ ሙሉ ሙሉ ስልሽ
እኔ አልነበርኩም ወይ ጠያቂም ወቃሽሽ
ለአንቺ ገላ መዉደቅ ሳለዉ አስታማሚዉ
የት ዉለሽ ማን ቀርቦሽ አቦሉን ካደምሽዉ

አፍቅሮሽ ስንቱን ባዬ ጎኔ
እንዴት ክስ መጥሪያ አመጣሽ ለኔ
አፍቅሮሽ ስንቱን ባዬ ጎኔ
እንዴት ክስ መጥሪያ አመጣሽ ለኔ

እስኪ ዶሴዉ ይዉጣ የምጠየቅበት
ወንጀሌን ሳላዉቀዉ እኔ አልቀጣበት እኔ አልቀጣበት
በማላዉቀዉ ጉዳይ ከመሰላት ዉላ
የተከሰስኩ እኔ የደፈራት ሌላ የደፈራት ሌላ

እኔን የሚያሳማኝ ያስጠየቀኝ ነገር
ድፍን የሀገሩን ወንድ አይቀር ከማስጠርጠር
ምነዉ ጉድ አመጣ ለአንቺ መታመኔ
ሲሞላ ከሌላዉ ሲጎልብሽ ከእኔ

እይ አይ አሃሃሃይ
ያረግሽኝን ነገር ባምንም አቅልዬልሽ
ለኋላስ ኑሯችን እንዴት ነዉ የማምንሽ
እኔ ባላረኩት ሸምጠሸ ከዋሸሽ
ልቤ እንዴት ይታረቅ ከጅምሩ ጎለሸ

አጋጥሞት ሳለ የሰረቀዉ
ጭምቱን ጉዳዩ አስጠየቀዉ
አጋጥሞት ሳለ የሰረቀዉ
ጭምቱን ጉዳዩ አስጠየቀዉ
አጋጥሞት ሳለ የሰረቀዉ
ጭምቱን ጉዳዩ አስጠየቀዉ



Credits
Writer(s): Elias Woldemariam, Tsegaye Deboch
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link