Kaba

ካባ ጣሉላት ከላይ ይታይ ውበቷ
የሰርጓ ቀን ነው ዛሬ በይ ኩሪ እናቷ
በማር በወተት አርገው አሳድገዋት
ኩለው ኳኩለው ደሞ "ሆ" ብለው ዳሯት

ወግ ነውና ሲዳሩ ማልቀስ
ቅር ቢለው ሆዷን ግን ደስደስ
"አንሰጣትም" ቢሉ እንዲህ በቀላሉ
በሩን ይዘው ሃይ ሎጋ ቢሉ

ሃይ ሎጋዬ እያለ ሲመጣ ሰርገኛ
በሩን ይዘን ስንል "አናስገባም እኛ"
አሸዎይና ቢሉ ይዞ መገኘት
እንዲህ በቀላሉ አንሰጥም ማለት
ሃይ ሎጋው ሽቦዬ
ሃይ ሎጋው ሽቦ
ሃይ ሎጋው ሽቦዬ
ሃይ ሎጋው ሽቦ
እና ና ና ና ና ናና ኤዬዬዬ

የሙሽራዬ እናት ውጪ ተከሰሻል
የሙሽራዬ እናት ውጪ ተከሰሻል
ይቺን መሳይ ቆንጆ ማን ውለጅ ብሎሻል
ሆሆ ሆሆ ሆሆሆ

ሸብ አድርገን በእልልታ እንሸኛታ
ክንዴ አድርገው መታ መታ እንዳትረታ
ሸብ አድርገን በእልልታ እንሸኛታ
ክንዴ አድርገው መታ መታ እንዳትረታ ሆ
ክንዴ አድርገው መታ
እንዳትረታ ሆ ክንዴ አድርገው መታ
እንዳትረታ ሆ ክንዴ አድርገው መታ
እንዳትረታ ሆ ክንዴ አድርገው መታ
እንዳትረታ ሆ ክንዴ አድርገው መታ
መታ መታ
እንዳትረታ
መታ መታ
እንዳትረታ
እና ና ና ና ና ናና ኤዬዬዬ ሆሆሆሆ

ጫኑት ሰጋር ፈረሴን ልጓም ግላሱን
አማላጅ ልከን አንዴ አውቀናል መልሱን
የጣልነው ጥሎሽ መጠን ቢበዛ ቢያንስም
አንዴ መጥተናል በቃ አንመለስም

ወግ ነውና ቤቷ ሲደረስ
ሆ በል ሚዜ ድንኳኑ እስኪፈርስ
አንሰጣትም እንዲህ በቀላሉ
የኔ ወገን "ሃይ ሎጋ" ቢሉ

ሃይ ሎጋ በል ልቤ ጣሰውና ዳሱን
ትክሳለህ ያኔ ስትጠራ መልሱን
ሲቀላቀል ሃሙስ ወገኗ ከኔ
ያንተ ናት ልጅቷ ኮራ በል ያኔ
ሃይ ሎጋው ሽቦዬ
ሃይ ሎጋው ሽቦ
ሃይ ሎጋው ሽቦዬ
ሃይ ሎጋው ሽቦ
እና ና ና ና ና ናና ኤዬዬዬ

የሙሽራዬ እናት ውጪ ተከሰሻል
የሙሽራዬ እናት ውጪ ተከሰሻል
ይቺን መሳይ ቆንጆ ማን ውለጅ ብሎሻል?
ሆሆሆሆሆሆሆ

ሸብ አድርገን በእልልታ እንሸኛታ
ክንዴ አድርገው መታ መታ እንዳትረታ
ሸብ አድርገን በእልልታ እንሸኛታ
ክንዴ አድርገው መታ መታ የታል እስክስታ
ክንዴ አድርገው መታ መታ እንዳትረታ ሆ
ክንዴ አድርገው መታ
እንዳትረታ ሆ ክንዴ አድርገው መታ
እንዳትረታ ሆ ክንዴ አድርገው መታ
እንዳትረታ ሆ ክንዴ አድርገው መታ
መታ መታ
እንዳትረታ
መታ መታ
እንዳትረታ
እና ና ና ና ና ናና ኤዬዬዬ

እንዲያ እንዲያው ዘመዴ ካባ ልበሽ በሏት እቴን
የልቤን ሙሽራዬ????
(እንዲያ እንዲያው ዘመዴ ካባ ልበሽ በሏት እቴን)
(የልቤን ሙሽራዬ????)
እንዲያ እንዲያው ዘመዴ ካባ ልበሽ በሏት በቃ
ከእናት አባት ኑሮ ከእንግዲህ አበቃ
(እንዲያ እንዲያው ዘመዴ ካባ ልበሽ በሏት በቃ)
(ከእናት አባት ኑሮ ከእንግዲህ አበቃ)
(ካባ)
(ካባ)
(ካባ) ጣሉባት
(ካባ) ጣሉባት
(ካባ) ጣሉባት
(ካባ) ጣሉባት
(ካባ) ጣሉባት
(ካባ) ጣሉባት
(ካባ) ጣሉባት
(ካባ) ጣሉባት
(ካባ) ጣሉባት
(ካባ) ጣሉባት
(ካባ)
(ካባ)
(ካባ) ጣሉባት
(ካባ) ጣሉባት
(ካባ) ጣሉባት
(ካባ) ጣሉባት
(ካባ) ጣሉባት
(ካባ) ጣሉባት



Credits
Writer(s): Teddy Afro
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link