Endegebsu Zala

እንደ ገብሱ ዛላ የኔዓለም
ፀጉሯ ተጎንጉኖ
መላው ሰውነቷ የኔዓለም
በመውደድ ተክኖ

አይነኮኮብ ጉብል የኔዓለም
የደስደስ የዋጣት
አስታውላኝ ሄደች የኔዓለም

የተዋበች ወጣት

የዘንድሮ ክረምት
አጉረመረመና
ሐምሌና ነሐሴ
አጥግቦታልና
አሳየኝ ይሄ ዓመት አሄ
ያቺን መልከ ቀና
እንዲህም አልነበር
ያቻምና ሃሳቤ
እንዲህም አልነበር
ያቻምና ሃሳቤ
እንደው በቆንጆ ልጅ አሄ
ተጨነቀ ልቤ
ዉበት አይቶ ማለፍ
እኔን መች ቸገረኝ
ዉበት አይቶ ማለፍ
እኔን መች ቸገረኝ
አሸነፈኝ ቃሏ ብታነጋግረኝ

እንደ ገብሱ ዛላ የኔዓለም
ፀጉሯ ተጎንጉኖ
መላው ሰውነቷ የኔዓለም
በመውደድ ተክኖ

አይነኮኮብ ጉብል የኔዓለም
የደስደስ የዋጣት
አስታውላኝ ሄደች የኔዓለም
የተዋበች ወጣት
ሸጋ የለም ብዬ

አውነት ነው ተብሎ
ቆንጆ የለም ብዬ
እውነት ነው ተብሎ
ጉድ አረገኝ አባይ አሄ
ጠምበለል አብቅሎ
ሐምሌና ነሐሴ

አልፎ አልቆ ወራቱ
ሐምሌና ነሐሴ
አልፎ አልቆ ወራቱ
በጋውም ደረሰ አሄ
ተሸኘ ክረምቱ
ያችስ የፍቅር ሰው

ምነው ታዲያ አትመጣም
ያችስ የፍቅር ሰው

ምነው ታዲያ አትመጣም
እያየ ልበል አሄ
ልቤ እየተቀጣም

ኦሆ...
አሀሀሀሀሀሀ...

እንደ ገብሱ ዛላ የኔዓለም

ፀጉሯ ተጎንጉኖ
መላው ሰውነቷ የኔዓለም
በመውደድ ተክኖ

አይነኮኮብ ጉብል የኔዓለም
የደስደስ የዋጣት

አስታውላኝ ሄደች የኔዓለም
የተዋበች ወጣት
ዘመድ ተሰብስቦ
ወገን አለኝ ብዬ
ዘመድ ተሰብስቦ

ወገን አለኝ ብዬ
ቤቱ ባደስ ደምቆ አሄ
ፍርዳየን ጥዬ

ከሰው መጫወቱን
ሆዴ እየተመኘ

ከሰው መጫወቱን
ሆዴ እየተመኘ
ደሞ ከዳኝ ልቤ አሄ
ወደ አንቺው ተሸኘ

አይግጠም ነው እንጅ
መቼም ከገጠመ
ልብ እንደ ሁዳዴ
እየቆረጠመ
የዞረ ያስፈታል አሄ
የተጠመጠመ

እንደ ገብሱ ዛላ የኔዓለም
ፀጉሯ ተጎንጉኖ
መላው ሰውነቷ የኔዓለም
በመውደድ ተክኖ

አይነኮኮብ ጉብል የኔዓለም
የደስደስ የዋጣት
አስታውላኝ ሄደች የኔዓለም
የተዋበች ወጣት
አስታውላኝ ሄደች የኔዓለም
የተዋበች ወጣት
አስታውላኝ ሄደች የኔዓለም
የተዋበች ወጣት
አስታውላኝ ሄደች የኔዓለም
የተዋበች ወጣት



Credits
Writer(s): Elias Woldemariam, Yilma G/ab
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link