Meshe Dehina Ederu

መሸ ደህና እደሩ ናፍቆት ነው ልማዴ
መቼም መተው እሷን አያውቅበት ሆዴ
ለታቦት ይሳላል የተጨነቀ ሰው
ማን አለኝ እንዳንቺ ነብሴን የወረሰው
ኮኮብ ተገለጠ ተሸኘ ጸሃይ
ልቤ ረጋ ሳይል አይኔ ሰው ሳያይ
እሷም አልተገኘች ብደክም ብለፋ
ፍቅር ሰሞን ነበር አጣጩ ባይጠፋ
መሸ ደህና እደሩ ናፍቆት ነው ልማዴ
መቼም መተው እሷን አያውቅበት ሆዴ
ለታቦት ይሳላል የተጨነቀ ሰው
ማን አለኝ እንዳንቺ ነብሴን የወረሰው
የመውደዴን ሚስጥር እንዴት ልሸፍነው
ማናገር ይወዳል መለየት ክፉ ነው
አንቺማ የሆድሽን መቼ ተነፈሽው
ዝም ብለሽ አይደል ወይ ጥለሽኝ የሄድሽው
መሸ ደህና እደሩ ናፍቆት ነው ልማዴ
መቼም መተው እሷን አያውቅበት ሆዴ
ለታቦት ይሳላል የተጨነቀ ሰው
ማን አለኝ እንዳንቺ ነብሴን የወረሰው
ብርዱ እየበረታ በግንቦት በሰኔ
ምነው በክረምቱ ትርቂያለሽ ካይኔ
እስኪ ልሂድ ገዳም ልግባ ልመንኩሰው
አንቺ ስምም የለሽ ትደርሻለሽ ከሰው
ትደርሻለሽ ከሰው
ትደርሻለሽ ከሰው



Credits
Writer(s): Elias Woldemariam, Yilma G/ab
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link