Eyasigeremegne

እያስገረመኝ ፡ እያስደነቀኝ
ብዙ ፡ ዓመት ፡ አለፈ ፡ ጌታ ፡ እየረዳኝ
ምህረቱ ፡ በዛ ፡ ድንቁ ፡ በህይወቴ
ለእኔስ ፡ ተለየብኝ ፡ ጌታ ፡ መድኃኒቴ

አለኝ ፡ ብዬ ፡ ምኮራበት
ለክፉ ፡ ቀኔም ፡ ምደገፍበት
ወረት ፡ አያውቀው ፡ እስካሁን ፡ ድረስ
ፍቅሩ ፡ እውነተኛ ፡ የልብ ፡ የሚያደርስ

እዚህ ፡ እደርሳሁ ፡ ብዬ ፡ አስቤ ፡ አላውቅም
ከቶ ፡ በእኔ ፡ ጉልበት ፡ የሚቻል ፡ አይደለም
የሚሆን ፡ አይደለም
ጌታ ፡ በፈቃዱ ፡ ይህን ፡ ካደረገው
ከመገረም ፡ ውጪ ፡ ሰዎች ፡ ምን ፡ እላለሁ
እኔ ፡ ምን ፡ እላለሁ

እንዲህ ፡ እሆናለሁ ፡ ብዬ ፡ አስቤ ፡ አላውቅም
ከቶ ፡ በእኔ ፡ ጉልበት ፡ የሚቻል ፡ አይደለም
የሚሆን ፡ አይደለም
ጌታ ፡ በፈቃዱ ፡ ይህን ፡ ካደረገው
ከመገረም ፡ ውጪ ፡ ሰዎች ፡ ምን ፡ እላለሁ
እኔ ፡ ምን ፡ እላለሁ

ይገርማል (፪x) ፡ አሰራሩ ፡ ይገርማል
ማን ፡ ገምቶት ፡ ያወቃል
ይደንቃል (፪x) ፡ ያረገልኝ ፡ ይደንቃል
ማን ፡ ገምቶት ፡ ያወቃል

አይገርማችሁም ፡ ወይ ፡ ወገኖች ፡ በሙሉ
ጌታ ፡ ያደረገው ፡ ለእኔ ፡ ለምስኪኑ
እርሱ ፡ በእኔ ፡ ሊከብር ፡ መስዋቴን ፡ ወዶታል
በደረቁ ፡ አጥንቴ ፡ ዝማሬን ፡ ጨምሮአል

ይገርማል (፪x) ፡ አሰራሩ ፡ ይገርማል
ማን ፡ ገምቶት ፡ ያወቃል
ይደንቃል (፪x) ፡ ያረገልኝ ፡ ይደንቃል
ማን ፡ ገምቶት ፡ ያወቃል

እያስገረመኝ ፡ እያስደነቀኝ
ብዙ ፡ አመት ፡ አለፈ ፡ ጌታ ፡ እየረዳኝ
ምህረቱ ፡ በዛ ፡ ድንቁ ፡ በሕይወቴ
ለእኔስ ፡ ተለየብኝ ፡ ጌታ ፡ መድኃኒቴ

አለኝ ፡ ብዬ ፡ ምኮራበት
ለክፉ ፡ ቀኔም ፡ ምደገፍበት
ወረት ፡ አያውቀው ፡ እስካሁን ፡ ድረስ
ፍቅሩ ፡ እውነተኛ ፡ የልብ ፡ የሚያደርስ



Credits
Writer(s): Tekeste Getnet
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link