Meqbezbez Sabeza

መቅበዝበዝ ሳበዛ በዓለም ስዋትት
ክብር መስሎኝ ታይቶኝ ውርደት ሳካብት
በበደሌ ብዛት ሞት የሚገባኝን
ፀጋህን አብዝተህ በህይወት ኖርኩኝ
ዛሬ ለአንተ ቆሜ በአፌ እዘምራለሁ
ያዳንከውን አዳዳን ገድልህን አወራለሁ
ግነን በዓለማት ስምህ ከፍ ይበል
በእርግጥ ከዚህ በቀር የለም የምከፍልህ

አንተን ያገኘሁ ዕለት መንገዴ ተቃና
በእጆችህ መራኸኝ በህይወት ጎዳና
ምክርህ ሰው ያደርጋል የአንደበትህ ቃል
ፍቅርህ እንደ ጠል ነው ደረቁን ያጸድቃል

አንተን ያገኘሁ ዕለት መንገዴ ተቃና
በእጆችህ መራኸኝ በህይወት ጎዳና
ምክርህ ሰው ያደርጋል የአንደበትህ ቃል
ፍቅርህ እንደ ጠል ነው ደረቁን ያጸድቃል

ስንከራተት ሳለሁ በምድረ በዳ ላይ
የሚረዳኝ የለ ግራ ቀኜን አላይ
ባልጠበኩት ቦት ከሰማይ ድምጽ መጣ
እጁ እጄን ያዘ ተራራ አወጣኝ
አንተ የኔ እኮ ነህ ልጄ እወድሃለሁ
በእውነት ቃል አስቤ ለክብር ወልጄሃለው
ለዘላለም ፍቅሬ ከአንተ አትለይም
አለኝ ለዘላለም እኔ አልጥልህም

አንተን ያገኘሁ ዕለት መንገዴ ተቃና
በእጆችህ መራኸኝ በህይወት ጎዳና
ምክርህ ሰው ያደርጋል የአንደበትህ ቃል
ፍቅርህ እንደ ጠል ነው ደረቁን ያጸድቃል

እርጥበት የማያውቅ በድርቅ የደቀቀ
ህይወቴ ነበረ ከአጥንት የደረቀ
ከፍጥረቴ ሳለሁ የበረሀ ወይራ
መጠጊያን አገኘሁ በመልካሙ ስፍራ
ምሁሩን ሊያስቀና ምስኪኑን መረጠ
ከውርደት አንስቶ ለክብር አስቀመጠ
በእሱ ተተክዬ በመልካሙ ግንድ ዘር
ልምላሜን አገኘሁ ለዘላለም ይክበር

አንተን ያገኘሁ ዕለት መንገዴ ተቃና
በእጆችህ መራኸኝ በህይወት ጎዳና
ምክርህ ሰው ያደርጋል የአንደበትህ ቃል
ፍቅርህ እንደ ጠል ነው ደረቁን ያጸድቃል

ጠመዝማዛ ጉዞ ቁልቁለት ሳዘግም
ሞቴን ለማፋጠን ሀጢያትን ስቃርም
በጠላት ድለላ በእሱ ጦር ታጅቤ
ከፍቅር አባቴ ከአንተ ሲሸሽ ልቤ
እንደ ህፃን አርገህ በእርጋታ መከርከኝ
ሳላውቅ እንዳልጠፋ ፍቅርህ ሰበሰበኝ
አንተ ካስጠጋኸኝ የሚከሰኝ ማነው
ነጻ ያወጣኸኝ ከልብህ ወደኸኝ ነው

አንተን ያገኘሁ ዕለት መንገዴ ተቃና
በእጆችህ መራኸኝ በህይወት ጎዳና
ምክርህ ሰው ያደርጋል የአንደበትህ ቃል
ፍቅርህ እንደ ጠል ነው ደረቁን ያጸድቃል

አንተን ያገኘሁ ዕለት መንገዴ ተቃና
በእጆችህ መራኸኝ በህይወት ጎዳና
ምክርህ ሰው ያደርጋል የአንደበትህ ቃል
ፍቅርህ እንደ ጠል ነው ደረቁን ያጸድቃል



Credits
Writer(s): Yohannes Girma
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link