Tsedqun

አምላኬን ፡ ልፈልግ ፡ በጠዋት ፡ በማታ
ጽድቁን ፡ ብቻ ፡ ልራብ ፡ መሽቶም ፡ እስኪነጋ
አምላኬን ፡ ልፈልግ ፡ በጠዋት ፡ በማታ
ጽድቁን ፡ ብቻ ፡ ልራብ ፡ መሽቶም ፡ እስኪነጋ

ጽድቁን ፡ ነው ፡ ዛሬም ፡ እራቤ
ጽድቁን ፡ ነው ፡ ነገም ፡ ጥማቴ
ጽድቁን ፡ ነው ፡ ሁሌም ፡ እረሃቤ
የምድሩ ፡ ትርፍ ፡ ነው ፡ ለእኔ
ጽድቁን ፡ ነው ፡ ዛሬም ፡ እራቤ
ጽድቁን ፡ ነው ፡ ነገም ፡ ጥማቴ
ጽድቁን ፡ ነው ፡ ዛሬም ፡ እረሃቤ
የምድሩ ፡ ትርፍ ፡ ነው ፡ ለእኔ

በጉብዝና ፡ ወራት ፡ ፈጣሪን ፡ ማሰብ
ይሻል ፡ አይደለም ፡ ወይ ፡ ከዚህ ፡ ዓለም ፡ ነገር
ይሄ ፡ ሚስጥር ፡ ገብቶኝ ፡ የምድሩን ፡ ንቄያለሁ
ክብርህን ፡ ሳይ ፡ ብቻ ፡ እኔስ ፡ እጠግባለሁ

በጉብዝና ፡ ወራት ፡ ፈጣሪን ፡ ማሰብ
ይሻል ፡ አይደለም ፡ ወይ ፡ ከዚህ ፡ ዓለም ፡ ነገር
ይሄ ፡ ሚስጥር ፡ ገብቶኝ ፡ የምድሩን ፡ ንቄያለሁ
ጽድቁን ፡ ብቻ ፡ ሳስብ ፡ እኔስ ፡ እጠግባለሁ

አይበልጥም ፡ ወይ
ጌታ ፡ አይሻልም ፡ ወይ
አይበልጥም ፡ ወይ
ጌታ ፡ አይሻልም ፡ ወይ

ስለምድር ፡ ሳስብ ፡ ለሚያልፈው ፡ ስጨነቅ
ዓመታት ፡ አለፉ ፡ ብዙ ፡ ለፋሁ ፡ ደከምኩ
አሁን ፡ በልጦብኛል ፡ የላዩ ፡ ተስፋዬ
አይረባኝም ፡ አወቅኩ ፡ የምድሩን ፡ መቆፈሬ

ስለምድር ፡ ሳስብ ፡ ለሚያልፈው ፡ ስጨነቅ
ዓመታት ፡ አለፉ ፡ ብዙ ፡ ለፋሁ ፡ ደከምኩ
አሁን ፡ በልጦብኛል ፡ የላዩ ፡ ተስፋዬ
አይረባኝም ፡ አወቅኩ ፡ የምድሩን ፡ መቆፈሬ

አይበልጥም ፡ ወይ
ጌታ ፡ አይሻልም ፡ ወይ
አይበልጥም ፡ ወይ
ጌታ ፡ አይሻልም ፡ ወይ

አይበልጥም ፡ ወይ
ጌታ ፡ አይሻልም ፡ ወይ
አይበልጥም ፡ ወይ
ጌታ ፡ አይሻልም ፡ ወይ



Credits
Writer(s): Yohannes Belay
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link