Teketa

ተቀጣ

ስንት እየባከነ ልቤ እራሱን ጥሎ
ነተበ ሳሳልሽ አንቺን ተከትሎ
ካንቺ ወዲያ እያለ
እያለ ልቤ
እያለ
ክብሩን አውልቆ መሬት ላይ ጣለ
ጭንቁር ተስፋውን ደግሞ ደግሞ እየተከተለ
ካንቺ ወዲያ እያለ
እያለ ልቤ
እያለ

አሀ... አንደበቴ ስንቴ ዋሸ
አሀ... ከእውነታው እየሸሸ
አሀ... አንደበቴ ስንቴ ዋሸ

ተቀጣ ተቀጣ ልቤማ
እያለ ሰው አልሰማ

ልቤ እንደው ሞኝ ነው በተስፋ ይኖራል
ድከም ሲለው እንጂ የነገን ማን ያውቃል
ካንቺ ወዲያ እያለ
እያለ ልቤ
እያለ
ከራሱ ገዳም ቆፍሮ ገብቶ
አንቺን ለማትረፍ ደግሞ ደግሞ በቃሉ ፀንቶ
ካንቺ ወዲያ እያለ
እያለ ልቤ
እያለ

አሀ... አንደበቴ ስንቴ ዋሸ
አሀ... ከእውነታው እየሸሸ
አሀ... አንደበቴ ስንቴ ዋሸ

ተቀጣ ተቀጣ ልቤማ
እያለ ሰው አልሰማ

ፍሙን ይዤ የፍቅርን ንዳድ
ነጉጄ ባንቺው መንገድ
መመለሻው የጠፋኝ ነኝ
ምንስ ነው የሚያሽለኝ

ካንቺው ጋር ነው
ውሌማ ካንቺው ጋር ነው

ላይን ማልሞላ ምናንቴ ነገር
ፍቅር አደፋፍሮኝ ሰዶኝ ካንቺው መንደር
አልሰማ ብዬ ነግሮኝ ሙሉ ሀገር

ካንቺው ጋር ነው
ውሌማ ካንቺው ጋር ነው

ተቀጣ ተቀጣ ልቤማ
እያለ ሰው አልሰማ



Credits
Writer(s): Sami Dan
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link