Yene Bichegna

የኔ ብቸኛ

የትም ዞሬ ስደርስ ደጃፍ ግርጌ
እጣራለሁ ስምሽን ከፍ አድርጌ
ካለሽ መልካም ከሌለሽ ነው ጉዱ
በድን ቤትን ይከብዳል መልመዱ

አንቺ ሁሌ እኔኑ ጠባቂ
ቀን ይበራል አይተሽኝ ስትስቂ
ያኔ ሁሉም ለኔ ይስተካከላል
መኖርሽ ብቻ ያኖረኛል

ነብሴን ይዤ እንዳልሰጥሽ
አልተቻለኝም ላንድያ ልጅሽ
ፈጣሪ ይርዳኝ ዘመኔን እንዳይሽ

ማን አለኝ ካንቺ ሌላ የኔ ብቸኛ

በእውቀት ቀለም ብሆን የመጠኩኝ
በስልጣኔ ሀገር ያስጨነኩኝ
ይሄ ሁሉ አንቺን መች ሊገርምሽ
ሁሌም ልጅ ነኝ እኔ ላንቺ ልጅሽ

በመንገዴ ፀሎትሽ ይቀድማል
ስንቱን ችግር ይዞ ያሻግረኛል
ምንም ብሆን ነብስያሽ ይነግረኛል
ስለኔ ብለሽ ስንቱ ውስጥ ገብተሻል

ነብሴን ይዤ እንዳልሰጥሽ
አልተቻለኝም ላንድያ ልጅሽ
ፈጣሪ ይርዳኝ ዘመኔን እንዳይሽ

ማን አለኝ ካንቺ ሌላ የኔ ብቸኛ

ነብስን በሚገርፈው በሀሩር በብርዱ
ጠብ የሚል ባይገኝ ባይቀናም መንገዱ
አንቺ ግን ስለኔ ሁሉንም ቧጠሻል
ፍቅርሽ ወሰን የለው ምንስ ያግድሻል

ልጄ ልጄ እያልሽ ስላንቺ ሳትኖሪ
ቤቱ እንዳይጓደል ቀልጠሽ የምትበሪ
ውለታሽ ቢበዛ አንድ ሆነ ፀሎቴ
አንቺን ያቆይልኝ ያኑርሽ እናቴ እማማ

ኡ እናትዬ ማማዬ...
ኡ እናትዬ...

ማን አለኝ ካንቺ ሌላ የኔ ብቸኛ



Credits
Writer(s): Sami Dan
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link