Endemelhik

መሬት የተኛ ሰው እወድቃለሁ ብሎ ከቶ እንደማይሰጋ
በእቅፍህ ስሆን እንዲያ ነው የማምንህ ልቤ የሚረጋጋ
ጸንቼ ቆሜአለሁ በማዕበሉ ላይ ቃልህን አምኜ
እንደማትጥለኝ እንደማትተወኝ እርግጠኛ ሆኜ

ልክ እንደ መልህቅ ወደ ውሀው ገብቶ
መርከብን እንደሚይዝ እንዳይወድቅ አፅንቶ
በሚናወጥ አለም እንዳልቀር ወድቄ
ህይወቴን {ዘመኔን} የያዝከው አንተ ነህ {ኢየሱስ}መልህቄ

ዝብርቅርቅ ህይወቴ በበዛልኝ ፍቅርህ በምህረትህ ቀንቷል
የትናንት ችግሬ ዳግም ላይመለስ ታሪክ ሆኖ ቀርቷል
ድኜ ቀርቼአለሁ ያለ አንዳች ምልክት ያለ አንዳች ጠባሳ
ዘመኔ ለምልሟል ከመልካምነትህ ካንተው የተነሳ

ልክ እንደ መልህቅ ወደ ውሀው ገብቶ
መርከብን እንደሚይዝ እንዳይወድቅ አፅንቶ
በሚናወጥ አለም እንዳልቀር ወድቄ
ህይወቴን {ዘመኔን} የያዝከው አንተ ነህ {ኢየሱስ}መልህቄ

በውጣ ውረዱ በኑሮ ስንክሳር
ከቶ አልናወጥም ስላለህ ከእኔ ጋር
በውጣ ውረዱ በኑሮ ስንክሳር
ከቶ አልናወጥም ስላለህ ከእኔ ጋር

ልክ እንደ መልህቅ ወደ ውሀው ገብቶ
መርከብን እንደሚይዝ እንዳይወድቅ አፅንቶ
በሚናወጥ አለም እንዳልቀር ወድቄ
ህይወቴን {ዘመኔን} የያዝከው አንተ ነህ {ኢየሱስ}መልህቄ



Credits
Writer(s): Ebba Daniel Deressa
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link