Endedrouachin

ፍቅርሽ እያሳየኝ ነው ማላውቀውን ደስታ
ደግሞም ያሰማኛል የስንቱን አሉባልታ
እኔ ለአንቺ ብለፋ ምን አለ! ምን አለ!
አንድ ግዜ እንጂ ሁለት ህይወት የለ
አንድ ግዜ እንጂ ሁለት የሞተ የለ

መዳከሜን አይቶ ወዳጅ ዘመድ ራቀኝ
ተስፋ ቤቴ ጠፋ ልቤም ተጨነቀ
ግን ጥሎ የማይጥለው ይመስገን ፈጣሪ
የውስጤን አየና ሰጠኝ ጥሩ አፍቃሪ
መዳከሜን አይቶ ወዳጅ ዘመድ ራቀኝ
ተስፋ ቤቴ ጠፋ ልቤም ተጨነቀ
ግን ጥሎ የማይጥለው ይመስገን ፈጣሪ
የውስጤን አየና ሰጠኝ ጥሩ አፍቃሪ

ማን ያቀናውን ማን ያዝበታል
ለአንቺ ነው ልቤ ለፍተሽበታል
ሃቅ ልናገር ይሉኝታ ሞቷል
ማን ያቀናውን ማን ያዝበታል
ለአንቺ ነው ልቤ ለፍተሽበታል
ሃቅ ልናገር ይሉኝታ ሞቷል
ዬዬዬ... ይሉኝታ ሞቷል

ፍቅርሽ እያሳየኝ ነው ማላውቀውን ደስታ
ደግሞም ያሰማኛል የስንቱን አሉባልታ
እኔ ለአንቺ ብለፋ ምን አለ! ምን አለ!
አንድ ግዜ እንጂ ሁለት ህይወት የለ
አንድ ግዜ እንጂ ሁለት የሞተ የለ

አይዞህ አይዞህ እያልሽ ይኸው ሁሉም አለፈ
ለኔ ህይወት መሳካት ያንቺ ውበት ረገፈ
ዛሬ ዘመድ ነኝ ባይ ያሻውን ቢያወራ
ልቤ ላንቺ ብቻ ነው እንዳትሰጊ አደራ
አይዞህ አይዞህ እያልሽ ይኸው ሁሉም አለፈ
ለኔ ህይወት መሳካት ያንቺ ውበት ረገፈ
ዛሬ ዘመድ ነኝ ባይ ያሻውን ቢያወራ
ልቤ ላንቺ ብቻ ነው እንዳትሰጊ አደራ

ምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ
ሚደክመው ልብሽ ሚያወራው ሌላ
የታለ ይሉኝታ ከአሁን በኋላ
ምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ
ሚደክመው ልብሽ ሚያወራው ሌላ
የታለ ይሉኝታ ከአሁን በኋላ

ማን ያቀናውን ማን ያዝበታል
ለአንቺ ነው ልቤ ለፍተሽበታል
ሃቅ ልናገር ይሉኝታ ሞቷል
ማን ያቀናውን ማን ያዝበታል
ለአንቺ ነው ልቤ ለፍተሽበታል
ሃቅ ልናገር ይሉኝታ ሞቷል



Credits
Writer(s): Abdu Kahssay
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link