Tirulgn

ንዴት ብስጭቴ ትግስ አሳጣ እንጂ እንዳልመልሰዉ
እንዴት ብዬ ልጥራዉ እኔዉ ወስኜ የሸኘሁትን ሰዉ
ለስህተቴ ይቅርታ ብላችሁ
እናንተዉ ጥሩልኝ ሄዳችሁ ተጨነኩላችሁ

ንዴት ብስጭቴ ትግስ አሳጣ እንጂ እንዳልመልሰዉ
እንዴት ብዬ ልጥራዉ እኔዉ ወስኜ የሸኘሁትን ሰዉ
ለስህተቴ ይቅርታ ብላችሁ
እናንተዉ ጥሩልኝ ሄዳችሁ ተሸነፍኩላችሁ

ነገር ያላደራ ቂም ያልቋጠረ ሰዉ
ሌላም ይናገራል ድንገት ሆድ ከባሰዉ
ግልፍ ይልበታል ሲናደድ አንድ አፍታ
ሲሰክን ይቋጫል የማታ የማታ የማታ የማታ
እኔ ስቀዘቅር ተቃጥሎ በተራዉ
በፀፀት መንደዴን አይሰማኝ ባወራዉ
ይቅርታ ልጠይቅ ቀርቤ እንዳወጋዉ
ምን መላ ልፈልግ በምን ላረጋጋዉ
በምን ላረጋጋዉ

ቁጣ ከሌለበት መዋደድ አንዳንዴ
ኩሪፍያ ከሌለበት መፋቀር አንዳንዴ
የአፍቃሪ ልብ እንዴት ይለካል
ሁል ጊዜ ሳቅ እንዴት ይሳካል
ተመለስ ተመለስ ተመለስ የኔ አካል
ተመለስ ተመለስ ተመለስ የኔ አካል
ተመለስ የኔ አካል

ንዴት ብስጭቴ ትግስ አሳጣ እንጂ እንዳልመልሰዉ
እንዴት ብዬ ልጥራዉ እኔዉ ወስኜ የሸኘሁትን ሰዉ
ለስህተቴ ይቅርታ ብላችሁ
እናንተዉ ጥሩልኝ ሄዳችሁ ተጨነኩላችሁ
ንዴት ብስጭቴ ትግስ አሳጣ እንጂ እንዳልመልሰዉ
እንዴት ብዬ ልጥራዉ እኔዉ ወስኜ የሸኘሁትን ሰዉ
ለስህተቴ ይቅርታ ብላችሁ
እናንተዉ ጥሩልኝ ሄዳችሁ ተሸነፍኩላችሁ

ማመዛዘኛዬን ድንገት ተነጥቄዉ
ጉድ ሆንኩኝ እንዳይቀርብ አርቄዉ
ትዕግስት የነሳኝን ያን አጉል ክፉ ቀን
ሳስብ ይገለኛል የቁጭት ሰቀቀን የቁጭት ሰቀቀን
ክፉ ሳይናገር ቆጥቦ አንደበቱን
እንዳቀረቀረ ሲሄድ ደፍቶ አንገቱን
ጓዙን አስጠቅልዬ ሸኝቼም አልረሳዉ
እኖራለሁ እንጂ ስሙን ሳነሳሳዉ
ስሙን ሳነሳሳዉ

አብሬዉ እያለዉ ብዙም ያልታወቀኝ
የናፍቆቱ ጉልበት አየሁት ሲርቀኝ
ጸጸት ብቸኝነት ሲያደቀኝ
ሳቅ ጨዋታ ደስታ ሲርቀኝ
ቤቴም ነፍ አዉጥቶ እሱን ሲጠይቀኝ
ምን ልልስለት ከየት ላምጣዉ ጨነቀኝ
ከየት ላምጣዉ ጨነቀኝ

ቁጣ ከሌለበት መዋደድ አንዳንዴ
ኩሪፍያ ከሌለበት መፋቀር አንዳንዴ
የአፍቃሪ ልብ እንዴት ይለካል
ሁል ጊዜ ሳቅ እንዴት ይሳካል
ተመለስ ተመለስ ተመለስ የኔ አካል
ተመለስ ተመለስ ተመለስ የኔ አካል
ተመለስ የኔ አካል

ተመለስ ተመለስ ተመለስ የኔ አካል
ተመለስ ተመለስ ተመለስ የኔ አካል
ተመለስ የኔ አካል



Credits
Writer(s): Hamelmal Abate
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link