Yazo Enba

የትኛዉ ሰዉ ነዉ አታላይ የትኛዉ ጥሩ
ህይወትን መስጠት ይከብዳል ካልፀና ፍቅሩ
የትኛዉ ሰዉ ነዉ አታላይ የትኛዉ ጥሩ

ህይወትን መስጠት ይከብዳል ካልፀና ፍቅሩ
አንተየዋ አንተየዋ ሆይ
ልቤን ጥዬ ልመንብህ ወይ
የመዉደዴ የፍቅሬ ፅሀይ
ልተማመን ልጠብቅህ ወይ
አንተየዋ አንተየዋ ሆይ
ልቤን ጥዬ ልመንብህ ወይ
የመዉደዴ የፍቅሬ ፅሀይ
ልተማመን ልጠብቅህ ወይ
እሽ ልብ በልና አድምጠኝ ከአንጀትህ ያለፈ ታሪኬን

ከአንድም ሁለት ሶስት ጊዜ አፍቅሬ ማጣቴን ወዶ መከዳቴን
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በኤኔ ላይ ዉል ይላል ግፍና ጭካኔ
የሚቀርበኝን ሁሉ እጠራጠር ጀመር ምን ተሻለኝ እኔ
እኔማ ልቀጣ ካለፈዉ አያርመኝ
የዚያኛዉ ሲገርመኝ እሄኛዉ ደገመኝ
ይሄንን ሁሉ ሰምቶ ሶስተኛዉ ሰዉ ሲገባ
ተካስኩኝ ብዬ ነበር የአዞ እምባዉን ሲያነባ
ተካስኩኝ ብዬ ነበር የአዞ እምባዉን ሲያነባ
ለካስ ጥፋቴ ኖሯል ስላለፈዉ ማዉራቴ
እኔስ የልቤን ነበር ግን ጐዳኝ ግልፅነቴ
እኔስ የልቤን ነበር ግን ጐዳኝ ግልፅነቴ

የትኛዉ ሰዉ ነዉ አታላይ የትኛዉ ጥሩ
ህይወትን መስጠት ይከብዳል ካልፀና ፍቅሩ
የትኛዉ ሰዉ ነዉ አታላይ የትኛዉ ጥሩ
ህይወትን መስጠት ይከብዳል ካልፀና ፍቅሩ
አንተየዋ አንተየዋ ሆይ
ልቤን ጥዬ ልመንብህ ወይ
የመዉደዴ የፍቅሬ ፅሀይ
ልተማመን ልጠብቅህ ወይ
አንተየዋ አንተየዋ ሆይ

ልቤን ጥዬ ልመንብህ ወይ
የመዉደዴ የፍቅሬ ፅሀይ
ልተማመን ልጠብቅህ ወይ
ከአንጀትህ ካፈቀርከኝ ያልጠገገ ቁስሌን አድርቅልኝ እንጂ
ምን ይፈይድልኛል እንባዬን የማይጠርግ የአንድ አፍታ ወዳጅ
የተወጋሁበትን የክዳት አንካሴ ጦሩ ሳይነቀል
በበደል ላይ በደል እንዳትጨምርብኝ አድነኝ ከበቀል
ዉስጤን ገልፀህ እየዉ ምኔን እንደሚያመኝ
የልቤን ስብራት በፍቅርህ አክመኝ
ሁለንተናዬ ብዬ በፍቅርህ ፀንቻለዉ

ከሰዉ አንተን አምኜ ህይወቴን ሰጥቻለዉ
ከሰዉ አንተን አምኜ ህይወቴን ሰጥቻለዉ
ልቤም ልብህን አምኖ በፍቅርክ ይደላደል
በአንተ በቃሽ ይበለኝ ዳግመኛ እንግዲህ በደል
በአንተ በቃሽ ይበለኝ ዳግመኛ እንግዲህ በደል
የትኛዉ ሰዉ ነዉ አታላይ የትኛዉ ጥሩ
ህይወትን መስጠት ይከብዳል ካልፀና ፍቅሩ
የትኛዉ ሰዉ ነዉ አታላይ የትኛዉ ጥሩ
ህይወትን መስጠት ይከብዳል ካልፀና ፍቅሩ
የትኛዉ ሰዉ ነዉ አታላይ የትኛዉ ጥሩ
ህይወትን መስጠት ይከብዳል ካልፀና ፍቅሩ
የትኛዉ ሰዉ ነዉ አታላይ የትኛዉ ጥሩ
ህይወትን መስጠት ይከብዳል ካልፀና ፍቅሩ
የትኛዉ ሰዉ ነዉ አታላይ የትኛዉ ጥሩ
ህይወትን መስጠት ይከብዳል ካልፀና ፍቅሩ
የትኛዉ ሰዉ ነዉ አታላይ የትኛዉ ጥሩ
ህይወትን መስጠት ይከብዳል ካልፀና ፍቅሩ



Credits
Writer(s): Hamelmal Abate
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link