Yerotuletin Yayutal

ከአንተ በፊት የቆሰሉ ብዙ አሉ ለወንጌሉ
እንደ እኔና እንዳንተ በነፃነት ዘመን ያልተፈጠሩ
ከአንቺ በፊት የተሰዉ ብዙ አሉ ለወንጌሉ
እንደ እኔና እንዳንቺ በነፃነት ዘመን ያልተፈጠሩ
ከኛ በፊት ብዙ አሉ የተሰዉ ለወንጌሉ
እንደኛ በነፃነት ዘመን ያልተፈጠሩ
ሳይሉ እጅ እግሬን ጨርቄን ማቄን በጽድቅ የኖሩ
በጌታ የተጉ ለጌታ የኖሩ በሰው የተጠሉ
አቤት የሮጡለትን ያዩታል ከወደላይ
የክብሩ ጌታ ሲያከብራቸው በሰማይ
አቤት ያዩታል ጌታን ፊት ለፊት
ሳያዩት ያመኑትን የናፈቁትን
በነፍሳቸው የጨከኑት
በስጋቸው ያከበሩት
አይገኝም አክሊላቸው
በሰማይ ነው ክፍያቸው
አቤት የሮጡለትን ያዩታል ከወደላይ
ሆነው የባርነት ባሪያ
ወጥተው ከሰውነት ተራ
የኔ ሚሉት የሌላቸው
ልሩጥ ለኔ ማያውቃቸው
ለወንጌል የቆሙ ለወንጌል የቀኑ
ገንዘብ ማይደፍራቸው ሰልፍ ብርታታቸው
አቤት የሮጡለትን ያዩታል ከወደላይ
የክብሩ ጌታ ሲያከብራቸው በሰማይ
አቤት ያዩታል ጌታን ፊት ለፊት
ሳያዩት ያመኑትን የናፈቁትን
በነፍሳቸው የጨከኑት
በስጋቸው ያከበሩት
አይገኝም አክሊላቸው
በሰማይ ነው ክፍያቸው
አቤት ያዩታል ጌታን ፊት ለፊት

ማነው? ታዲያ የዘመኔ አርበኛ
ለጌታ ነገር ያልተኛ
ብድራቱን እዚህ ያልተቀበለ
እውነት ለወንጌል የጀገነ
በነፃነት ዘመን ራሱን የሰዋ
ለጥቅም ያልኖረ በእምነቱ የፀና
ማነው የዘመኔ ወንጌል ነጋሪ
በተግባር የታየ የጽድቅ ተባባሪ
ያልሆነ በፍፁም የነፃነት ባሪያ
ከቶ ያልተገኘ እዚህ ሲሉት እዚያ
ማነው? የአቋም ሰው ዘመን ተሻጋሪ
ሰልፍ እየበረታ ወንጌሉን ዘማሪ
ማነው የዘመኔ ባለ አክሊል ተረኛ
ለራሱ ያልኖረ ከስጋው ጠበኛ
ሞትን ጥቅሜ ብሎ በነፍሱ የጨከነ
ግራ ቀኝ ያላየ ለቃሉ የታመነ
ማነው የዘመኔ አርበኛ ማነው
አቤት የሮጡለትን ያዩታል ከወደላይ
የክብሩ ጌታ ሲያከብራቸው በሰማይ



Credits
Writer(s): Samuel Alemu, Hanna Tekle, Yerotuletin Yayutal
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link