Fisehaye

የምፈልገውን ሁሉ ባገኝ
የምፈልገው ደስታ ጋር አልደርስም
ስደርስበት ይቀልብኛል
ሳልጠግበው ይሰለቸኛል
የኔ ክፍተት ሌላ ነው ብርም ወርቅም አይደለም
ኢየሱስ ነው ረሃቤ መንፈስ ነው ጥጋቤ

በህልውናህ ስር መሆን ባንተ መኖር ውሎ ማደር
በመገኘትህ የታሰበ ሰው ምንኛ የታደለ ነው
አስበኝ የኔን ልብ በህልውናህ በሚያፅናናው በመንፈስህ
ይህ ነው ጥማቴ ይህ ነው ጉጉቴ ክብርህን ማየት ነው መሻቴ
ትርጉም ለጠፋው ሕይወቴ
ምላሽ ሲታጣ ከሞላው ቤቴ
ለመኖር ስዝል ሲደክመኝ
ባዶነቴ ሲጮህብኝ
የኔ ክፍተት ሌላ ነው ያለኝ ነገር አይደለም
ኢየሱስ ነህ ረሃቤ መንፈስ ነው ጥጋቤ
በህልውናህ ስር መሆን ባንተ መኖር ውሎ ማደር
በመገኘትህ የታሰበ ሰው ምንኛ የታደለ ነው
አስበኝ የኔን ልብ በህልውናህ በሚያፅናናው በመንፈስህ
ይህ ነው ጥማቴ ይህ ነው ጉጉቴ
ክብርህን ማየት ነው መሻቴ
ህልሜ አንተን ማየት በኑሮዬ
ህልሜ አንተን ማየት ነው ጉጉቴ
የደስታዬ ልክ ሰላሜ የእርካታዬ ጥግ ፍስሃዬ ኢየሱስ
ይህ ነው ጥማቴ ይህ ነው ጉጉቴ
ክብርህን ማየት ነው መሻቴ
ህልሜ አንተን ማየት በኑሮዬ
ህልሜ አንተን ማየት ነው ጉጉቴ
የደስታዬ ልክ ሰላሜ የእርካታዬ ጥግ ፍስሃዬ ኢየሱስ
ይህ ነው ጥማቴ ይህ ነው ጉጉቴ ክብርህን ማየት ነው መሻቴ



Credits
Writer(s): Samuel Alemu, Hanna Tekle, Yerotuletin Yayutal
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link