Yalemikniyat

ስፈራ ስቸር ማልተነፍሰው ሚስጥሬ በዝቷል
እኔም ባልናገር የልብ ወዳጄ የውስጤን ያውቃል
እሱ እንደሚያውቀኝ ሰው አያውቀኝም እንጂ
መቆም አልችልም እንኳን በንጉስ በራሴም ደጅ
የምህረት ዐይኑ ዛሬም ያየኛል
አልሰለቸኝም ይፈልገኛል
የምህረት ዐይኑ ዛሬም ያየኛል
አልሰለቸኝም ይፈልገኛል
ፈላጊዬ መሀሪዬ
ኢየሱስ ወዳጄ
አይዞሽ ሚለኝ እኔን
ሚያበረታኝ ነው የልብ ወዳጄ
ኢየሱስ (×፫)

እንዳትወደኝ በመልካምነቴ
ይህ አይደለም ማንነቴ
እንዳትጠላኝ ደግሞ በጥፋቴ
ፍቅር ነህ አያስችልህም አባቴ
ያለምክንያት ወደህ በምክንያት አትጠላም
ለምህረትህ ስፍር መለኪያ የለውም
ያንተ ፍቅር መነሻው ከራስህ
የመውደድ ልብ የማያልቅብህ
ያለምክንያት ወደህ በምክንያት አትጠላም
ለምህረትህ ስፍር መለኪያ የለውም
ያንተ ፍቅር መነሻው ከራስህ
የመውደድ ልብ የማያልቅብህ የኔ ጌታ

ከወዳጅ ከፍቶ ልጅ ድርሻዬን ብሎ እርም እንዳላለ
አልመች ቢለው የሸፈተበት አባቴን አለ
አባትነቱን የበደል ብዛት በች ይሽረዋል
ሁሉን ረስቶ ደግሞ እንደገና ልጄ ይለዋል
የምህረት ዐይኑ ዛሬም ያየኛል
አልሰለቸኝም ይፈልገኛል
የምህረት ዐይኑ ዛሬም ያየኛል
አልሰለቸኝም ይፈልገኛል
ፈላጊዬ መሀሪዬ
ኢየሱስ ወዳጄ
አይዞሽ ሚለኝ እኔን
ሚያበረታኝ ነው የልብ ወዳጄ
ኢየሱስ (×፫)



Credits
Writer(s): Samuel Alemu, Hanna Tekle
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link