Selam Newe

መኖሪያዬ የዘላለም አምላክ
የአባቶቼ የነ ሙሴ አባት
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም
የሚያውቅልኝ እንደ አንተ አላገኝም
ብታድነኝም ባታድነኝም አንተ መልካም ነህ
ይህንን አድርግ ያንን አታድርግ መች ትባላለህ
ለአደራረግህ ማስተካከያ ከማንም አትሻም
ፍፁም በስራህ ፍፁም በምክርህ አትሳሳትም
ያስጨነቀኝ ቀንበሬ ውስጤን አንቆ የያዘው
ለኔ እንጂ ቢከብደኝ ኢየሱስዬ ላንተ እንዴት እንዲህ ቀላል ነው
የዛሬው ድቅድቅ ሌሊቴ ይገባሃል ሚስጥሩ
ፊትህን እያየሁ ዛሬም ግን እላለሁ ሰላም ነው
ሰላም ነው እላለሁ
በእጅህ የገባውን ነገሬን እያየሁ
ሰላም ነው እላለሁ
ውስጤ ሸክም አዝሎ እጅህን እያየሁ
አልገባሽ ቢለኝ ነገሩ ማዕበል ወጀቡን ፈርቼ
ውስጤን ብርዱ ተሰማኝ ሰው ነኝና ሰግቼ
ጉልበቴ እልሃለሁ ዛሬም አቅሜ አንተ ነህ አቤቱ
እምነቴ እንደው አልታመነም አይተኸኝል በብዙ
ግን እላለሁ
ሰላም ነው እላለሁ
ያደረክልኝን ትላንትን እያየሁ
ሰላም ነው እላለሁ
በዚህ አይቀጥልም ክብርህን አያለሁ
ሰላም ነው እላለሁ
ያደረክልኝን ትላንትን እያየሁ
ሰላም ነው እላለሁ
ይህም ሌሊት ያልፋል ክብርህን አያለሁ

ደህና ነው ካለች ሱናማዊቷ
የአንድ ልጇን ነፍስ አጥታው ከቤቷ
ታዲያ እንዴት አልል ሰላም ነው
ባለቤት አለኝ የኔ አይደለሁም
በትንሽ ትልቁ ብዙ ጭንቀቴ
መልስ እንዳይሆነኝ ለዘመመው ቤቴ
ተረድቻለሁ ይህን አውቂያለው
ነገሬን ሁሉ አስረክቤዋለው

መኖሪያዬ የዘላለም አምላክ
የአባቶቼ የነ ሙሴ አባት
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም
የሚያውቅልኝ እንደ አንተ አላገኝም
ብታድነኝም ባታድነኝም አንተ መልካም ነህ
ይህንን አድርግ ያንን አታድርግ መች ትባላለህ
ለአደራረግህ ማስተካከያ ከማንም አትሻም
ፍፁም በስራህ ፍፁም በምክርህ አትሳሳትም
ሰላም ነው (×፰)
አውጃለሁ ዛሬም መልካምነትህን ባልሞላው ነገሬ
ስንፍናን አልሰብክም እምነቴን አልጥልም ከንቱ ተናገሬ
ከአንተ በላይ ለኔ ለመጪው ዘመኔ እኔ አላውቅምና
መቆዘሜን ጥዬ ይህም ያልፋል ብዬ ልለፍ በምስጋና
ብርቱ ሰልፍ ሲሆን ሕይወቴ
እንድማር ነው አባቴ
ንፋሱ ሲያይል ሲበረታ
ድንቅህን ላይ ነው የማታ ማታ
ብርቱ ሰልፍ ሲሆን ሕይወቴ
ለትምህርቴ ነው አባቴ
ወጀቡ ቢያይል ቢበረታ
ግን ድሉ የኔ ነው የማታ ማታ
ሰላም ነው (×፰)



Credits
Writer(s): Samuel Alemu, Hanna Tekle
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link