Wa

ወይ ወይ ወይ ወይ
ዘንድሮ ነገሩ አስፈሪ
ቤቱን እረስቶ ውጪ አክባሪ
አባት ላገሩ የወደቀው ልጁ ግድ የለሽ የማይደንቀው
ሸክሙን ችሎ እያወቀው ዝም ስላለ የተናቀው
ወድቆ ያኖራት ነፃ ምድር እኔም ወድቄ ላልከፍል ብድር
ተያዥ የለኝ ምስክር ታሪኩን ወራሽ የነገን ፍሬ
እውነት እውነቱን ልንገራት ዛሬ
ምናል ብወድሽ በገዛ አገሬ
ያደግኩበት ብዙ ነው ዘሬ
የእናት ስጋት የአባት ፍራት ያገር ናፍቆት ወሞ ስደት

ጌቲ ⤵️
ፍቅርን ንቆ ለሚገፋ የከበረ ግን ሳይለፋ
የሰውን ላብ ለሚቀማው ያልሰራውን ለሚሻማው
ያልፋል ብሎ ለሚለፋው በየጫካው ለተገፋው
በረሀ ላይ ለቀረ ሰው የእግር ጉዞ ለጨረሰው

ቴዲ ⤵️
ሰው አያጣውም ማስመሰሉን
ውስጡ ጥቁር ፍም ከሰሉን ፈካ ብሎ መቃጠሉን
ማን ተናግሮ የስሜቱን
የላሊበላን ሚስጥር ተረስቶ ደራሽ ጠፋ ታሪክ አሽትቶ
ታሪኩ የኛ ተጵፎ በነጭ ግራ ተጋብቶ ከራሱ ሲጋጭ
ጠፍቶበት የፈጠራው ምንጭ
ስራ ቢጠፋ ስደት አማራጭ
ህመሜ ባሰ ከአምናው ዘንድሮ
ነጥቆ በል ከደሀ ጉሮሮ
ሰው ተቸግሮ ሙሰኛ ከብሮ የእጁን ያገኛል
ጊዜው ተቀይሮ
ተንኮል ቅናት ሀዘን ጥፋት ለራስ ማድላት
ይቁም ስርቆት

ጌቲ ⤵️
ፍቅርን ንቆ ለሚገፋ የከበረ ግን ሳይለፋ
የሰውን ላብ ለሚቀማው ያልሰራውን ለሚሻማው
ያልፋል ብሎ ለሚለፋው በየጫካው ለተገፋው
በረሀ ላይ ለቀረ ሰው የእግር ጉዞ ለጨረሰው

ቴዲ ⤵️
ድብቅ ያሉት ይፋ እስኪሆን ይፋ ያሉት እስኪደበቅ
በዝምታ ብቻ መርቀቅ ... በዝምታ ብቻ መድቀቅ
ይህን ጊዜ አገር መልቀቅ አገር ለቆ መነፋፈቅ

ተነፋፍቆ መነፋረቅ ... ተነፋርቆ መዘባረቅ
ተዘባርቆ መጠቋቆም ... ለራስ ትቶ ላገር መቆም
ላገር ጮሆ ለማስማማት የሰው ጆሮ መከራየት
ከፍቅር ጋር ማገናኘት ስራዬ ነው ተስፋ መስጠት
ወጣት እሳት ጥረት ጉልበት ተስፋ ትግስት ኩራት ድፍረት

ጌቲ ⤵️
ፍቅርን ንቆ ለሚገፋ የከበረ ግን ሳይለፋ
የሰውን ላብ ለሚቀማው ያልሰራውን ለሚሻማው
ያልፋል ብሎ ለሚለፋው በየጫካው ለተገፋው
በረሀ ላይ ለቀረ ሰው የእግር ጉዞ ለጨረሰው



Credits
Writer(s): Solomon Ambaw
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link