Edmea

በድንግዝግዝ አለም ብልጭታ አለ ግን ሩቅ ይመስላል
ሊይዝ ሊጨብጠው መንገድ የጀመረውን ሰው እውር ይመራዋል
አልችልም እራስን አጥቶ መኖር እራስን ጠልቶ ጠፋለው
አልችልም ተቀያይሞ መኖር አታሎ እፈራለው

(ጨለማ ነው)
(ጨለማ ነው)

እድሜ ተቆጥሮ ቢያልቅ ጊዜው
ዘመናት ቢያልፉ እንደወትሮው
አይቀርም እራስን ማየት ወደውስጥ
ያኔ ይቆጫል ሳይኖሩ መሞት

ዛሬ ታይቶ ነገ እንደሚጠፋ እንደ እንፋሎት ነው
ተው ያዝ እውነትን እንዳጥል ተንከባከበው
ማየትን እመርጣለው ወደውስጥ አሻግሬ ላገኘው
ፋኖሱ ሊጠፋ ቢል ዘይቱ ተንጠባጥቦ ሊያልቀው

(ግን እጓዛለው)
(ግን እጓዛለው)

እድሜ ተቆጥሮ ቢያልቅ ጊዜው
ዘመናት ቢያልፉ እንደወትሮው
አይቀርም እራስን ማየት ወደውስጥ
ያኔ ይቆጫል ሳይኖሩ መሞት

ተጉዤ ተጉዤ ደረስኩ መጨረሻ
ያየሗት ብልጭታ ሆነች ጨለማ
ሙጥጥ ብሎ አለቀ የያዝኩት እምነቴ
በሩ እንደተዘጋ ሞትን ፈርቼ



Credits
Writer(s): Dawit Belay
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link