ZAF

ተስፋ ተጥሎበት የት ይደርሳል ተብሎ
ኀላፊ አግዳሚው በርሱ ተገርሞ
ባፈራው ቅርንጫፍ ስንቱን አስጠልሎ
ይኖር ነበረ የኖረ መስሎ

ተቆረጠ በሰዎች እጅ ወደቀ
ተስፋ እንዳይኖረውም ተሰነጠቀ
መልሶ እንዳይበቅል ደግሞ እንዳይሆን ጥላ
በቅርንጫፎቹ መጥረቢያ ተሰራ

አይ አለማስተዋል ስር እየሰደዱ
ቅርንጫፉ እንዳይኖር ይቆረጣል ግንዱ
ቀንበጡ እረግፎ ጉቶ እየመሰለ
ግን እሚያስገርመው ስር ውስጥም ዘር አለ

ግን ደግሞ ይነሳል አይሞትም እሱ
መልሶ ያፈራል ከሞተው ክፍሉ
መልሶ ይመጣል ውሀን አሽቶ
አብዝቶ ያፈራል ከቀድሞ አብልጦ መውደቅ እንዳለ አለ ደግሞ መነሳት
ተስፋ አጥቶ ደግሞ ማግኘት መልሶ ተስፋን
አይቀርም ደርቆ አለ መልሶ ማፍራት
ዛሬ የጠፋው ነገ ደግሞ ይበራል

ሰዎች ቢሉት የሞተ የተላቀቀም ቢመስል ከፍጥረት ጎራ(ጎራ)
አይመለስ ብለው ለዘላለም አሸልቧል በቃ ለይቷል
ይሰማል መንፈሱ በህይወት ጎዳና ስሙን ሰምቶ ይወጣል(ጎበዝ ናውጣ)
ዳግም አንሰራርቶ ሙታንን ተላቆ (መጣ) ከህያዋን መንደር
ራሱን ሰቶ ለህይወትም ቃና
አሽብርቆ ይታይ የለ ገና
አልጨረሰም አለው አለው ሌላ
በዝቶለታ አለው ገና ገና
ቆሞ ይሄዳል እንዳዲስ ነው ሌላ
ከሞተበት ክፍል መቃብሩ ተከፍቶ ይወጣልና

አይ አለማስተዋል ስር እየሰደዱ
ቅርንጫፉ እንዳይኖር ይቆረጣል ግንዱ
ቀንበጡ እረግፎ ጉቶ እየመሰለ
ግን እሚያስገርመው ስር ውስጥም ዘር አለ

አይ አለማስተዋል ስር እየሰደዱ
ቅርንጫፉ እንዳይኖር ይቆረጣል ግንዱ
ቀንበጡ እረግፎ ጉቶ እየመሰለ
ግን እሚያስገርመው ስር ውስጥም ዘር አለ



Credits
Writer(s): Dawit Belay
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link