Musherit

ፍቅር ያልገባትን ወዳ ማታውቀዉን ውዱን
ሊያስረዳት ቢደክም ሊያሳያት የቆሰለውን ልቡን
ንጉስ ድል ቢያደርግ ቢያሸንፍ በብዙ ጦር ሜዳ
እልፍ ቢገድል ግን ሆነ የፍቅር እስረኛ

አይ! በቃህ ይቅርብህ ቢሉት
አትበጅህም አትድከም ተዋት
ባትረዳውም ሚሰጣትን ፍቅር
እሱ ግን መልሶ ነፍሱንም ሰጣት

ያኔ ቢገባት የሰጠው ያረገውን ሁሉ
ፍቅር ቢይዛት ወሰነች ልታገባው
ጥሎሽን ላከላት ፍቅሩ እንድትዋብለት
እሩቅ ሀገር ሄደ መኖሪያን ደግሞ ሊሰራላት

ውዷን ስጠብቅ ሙሽሪት ተውባ በቤት
ፍቅሯ ቢያረፍድ ቢቆይ ሳይመለስላት
እንደው ቢድክማት መጠበቅ ያንን ሁሉ ጊዜ
ልትፈልግ ብትወጣ ሰረቃት ያላትን ወንበዴ

አይ! በቃህ ይቅርብህ ቢሉት
አትበጅህም አትድከም ተዋት
ባትረዳውም ሚሰጣትን ፍቅር
እሱ ግን መልሶ ነፍሱንም ሰጣት

አይ! በቃህ ይቅርብህ ቢሉት
አትበጅህም አትድከም ተዋት
ባትረዳውም ሚሰጣትን ፍቅር
እሱ ግን መልሶ ነፍሱንም ሰጣት



Credits
Writer(s): Dawit Belay
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link