Yemechereshawa Se'at

የመጨረሻዋ ሰዓት

የመጨረሻዋ ሰዓት
የመጨረሻዋ ደቂቃ
አለፈች እኔን አስጨንቃ - እጅግ አስጨንቃ
ካይንሽ ላይ ያነበብኩት
ተስፋ እምነትሽ ወድቆ
ያ ሁሉ ትግስትሽም አልቆ - ያ ትግስትሽም አልቆ

ፍቅርሽን ያጣሁ ለት - ሆድዬ
መውደድሽን ያጣሁ ለት
ፍቅርሽን ያጣሁ ለት
ያኔ ነው እኔማ የተሰበርኩት

ፍቅርሽን ያጣሁ ለት - ኡ...
ያጣሁ ለት
ፍቅርሽን ያጣሁ ለት
ያኔ ነው እንደሰው መቆም ያልቻልኩት

የመጨረሻዋ ሰዓት
የመጨረሻዋ ደቂቃ
አለፈች እኔን አስጨንቃ - እጅግ አስጨንቃ
መርዶዬን ስትነግሪኝ
እኩል እኔም ነቃሁ
አይኔ ሲገለጥ እጅግ ፈራሁ - ለካስ ብቻዬን ነኝ ፈራሁ

ሁሌ ማይታረመው ይህ አንደበቴ
ቃላት የማይመርጠው ባዶ ጩኸቴ
አውቃለሁ ውዴ ስንቴ እንዳሳመመሽ እንደጎዳሽ
ከህሊናዬ ስመለስ ደግሞ
ሳስበው እየዘገነነኝ
ግን ደግሞ የማያርኝ ብኩን ነኝ

ይገባኛል እኔ ብዙ ሌላ ቅጣት
ግን ባይሆን ይሻል ነበር አንቺንስ ከኔ በማጣት
ስጋዬን ሰርስሮ ካጥንቴ የገባው
የህሊናዬ ቁስል አንቺ ላይ ያረኩት ነገር ነው

ፍቅርሽን ያጣሁ ለት - ሆድዬ
መውደድሽን ያጣሁ ለት
ፍቅርሽን ያጣሁ ለት
ያኔ ነው እኔማ የተሰበርኩት

ፍቅርሽን ያጣሁ ለት - ኡ...
...ያጣሁ ለት
ፍቅርሽን ያጣሁ ለት
ያኔ ነው እንደሰው መቆም ያልቻልኩት

ኦ... ኦድዬ... ፍቅርሽን ያጣሁ ለት



Credits
Writer(s): Sami Dan
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link