Hule Addis

በማለዳ ድምጼን ትሰማለህ
ውስጤን ሰላም ሐሴት ትሞላለህ
ከዙፋንህ ትመለከታለህ
የሚያስፈልገኝን ትሰጠኛለህ

በማለዳ አለሁ ትለኛለህ
ነፍሴን ከበረከትህ ታጠግባታለህ
ከዙፋንህ በጽድቅ ትፈርዳለህ
ያስጨነቀኝን ሸክም ትወስዳለህ

አያልቅብህ አያልቅብህ
ምህረት ቸርነትህ ምህረትህ
አያልቅብህ አያልቅብህ
ጸጋህ ስጦታህ ኧረ ደግ ነህ

ይገርመኛል እለት በእለት
የማይቋረጥ ጥበቃ ትኩረት
ከዛሬ ነገ ማይለዋወጥ
ጸንቶ የሚኖር ያንተ ማንነት

ይገርመኛል እንክብካቤህ
ከእናት ከአባት የሚበልጥ ፍቅርህ
ለዘለዓለም ማይለዋወጥ
የእውነት ልዩ ነው ያንተ ማንነት

ሁሌ አዲስ ነው ምህረትህ
ደግሞ አያልቅ ቸርነትህ
ለደካማው ኃይል ይሰጣል
የወደቀውን ያነሳል
አይቻለሁ ደግፈኸኝ
እንዳያጠፋኝ ወጀቡ
አቅም ሳጣ እጄን ይዘህ
ስታሻግረኝ ባህሩን

(ሁሌ አዲስ ነው ምህረትህ)
(ደግሞ አያልቅ ቸርነትህ)
ለደካማው ኃይል ይሰጣል
የወደቀውን ያነሳል
(አይቻለሁ ደግፈኸኝ)
(እንዳያጠፋኝ ወጀቡ)
አቅም ሳጣ እጄን ይዘህ
ስታሻግረኝ ባህሩን

አያልቅብህ አያልቅብህ
ምህረት ቸርነትህ ምህረትህ
አያልቅብህ አያልቅብህ
ጸጋህ ስጦታህ ኧረ ልዩ ነህ



Credits
Writer(s): Exodus Lambebo
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link