Sikelilign

የማልፈልገው ሰው በውስጤ አለ
አብሮኝ በሰላም በጤና እየኖረ
ከአምላኬ ሊያርቀኝ ምሎ ተገዝቶ
ሌተ ቀን ያደባል ባጎረስኩት ነክሶ
ስቀልልኝ
ስቀልልኝ

ግሩም ፈሪሳዊ ውጬን ብጠነቀቅ
ከክፉ ሰዎች አፍ ከዋዘኞች ብርቅ
ትልቁ ጠላቴ ልሸሸው የማልችለው
አብሮኝ የሚኖር ይኀው ስጋዬ ይኀው
ስቀልልኝ
ስጋዬን መሻቴት ስቀልልኝ
ስቀልልኝ

ሞት የሃጢአት ደመወዝ
የስጋዬ መዝዝ
ላንተ እንዳልታዘዝ
አያድርገኝ ስቀልልኝ
ቅዱስ የጽድቅ ባሪያ
የመንፈስ ማደሪያ
ልዑል ምታርፍበት
ንጹህ ልብን ፍጠርልኝ

መንፈስህ ያግኘኝ
ጸጋህ ብቻ ፍቅርህ ብቻ
ካንተ ጋር ልስማማ
እንዳልጠፋ ያዘኝ ጌታ

ያላንተ እንዳይሆን
የተናጠል ጉዞ
ኃይልህ በሌለበት
መልክ ብቻ ሆኜ ባዶ
አድርገኝ የጽድቅ ባርያ
የመንፈስ ማደሪያ
የሱስ የሱስ የሚሸት
የሚያፈራ በሁሉ ወቅት

መንፈስህ ያግኘኝ
ጸጋህ ብቻ ፍቅርህ ብቻ
ካንተ ጋር ልስማማ
እንዳልጠፋ ያዘኝ ጌታ

ስቀልልኝ
ስጋዬን መሻቴት ስቀልልኝ
ስቀልልኝ



Credits
Writer(s): Exodus Lambebo
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link